Print this page
Saturday, 22 June 2019 10:47

“የወገን ጦር” መፅሀፍ ዛሬ ይመረቃል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)


             በደርግ አገዛዝ የሁለተኛ ክ/ጦር አካል የሆነው የ12 ብርጌድ አባል በነበሩትና በከረንና በአካባቢው በ3ኛ ክቡር ዘበኛ ብርጌድ ተካትተው አስመራ ጭምር በተጓዙት ሻለቃ ማሞ ለማ የተፃፈውና ከንጉሳዊ አገዛዝ መገርሰስ እስከ ደርግ ያለውን እንዲሀሁም በውትድርና ህይወት ያሳለፉትንና የገጠማቸውን የሚያስታውሱበት” የወገን ጦር” መፅሐፍ ዛሬ ሳር ቤት አካባቢ በሚገኘው ኪንግስ ሆቴል ከቀኑ 9፡00 ጀምሮ ይመረቃል፡፡
በዕለቱ ሻለቃ ማሞ ተገኝተው መፅሐፉ እንዴትና ለምን እንደተፃፈ ለታዳሚ የሚገልፁ ሲሆን መፅሐፉን ከስነ ፅሁፋዊ ጥበቡ አኳያ ጋዜጠኛ ልጅ ወንድሜነህ፣ የሚዳስሰው ሲሆን አጠቃላይ የመፅሐፉን ግምገማ ዶ/ር ባለው እንደሚያቀርብና የጥያቄና መልስ ውይይት እንደሚኖር ሻለቃ ማሞ ገልፀዋል፡፡ መድረኩም በጋዜጠኛ ተፈሪ ዓለሙ ይመራል ተብሏል፡፡ 601 ገፅ ያለው መፅሐፉ፣ በ300 ብር ለገበያ ቀርቧል፡፡

Read 2419 times