Print this page
Sunday, 23 June 2019 00:00

የደራሲያን ማህበር የክረምት ስልጠና ሐምሌ 1 ይጀመራል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

ዓመታዊው የመፅሐፍት አውደ ርዕይ ሰኔ 24 ይከፈታል

            የኢትዮጵያ ደራሲያን ማህበር የክረምት የስነ ፅሁፍ ስልጠና ሐምሌ 1 ቀን 2011 እንደሚጀመር ማህበሩ አስታወቀ፡፡ በየዓመቱ ፍላጎት ላላቸው ሰልጣኞች የሚሰጠውና ዘንድሮ ለ7ኛ ጊዜ የሚካሄዴው የክረምት ስልጠናው እንደሁልጊዜው 60 ሰልጣኞችን ተቀብሎ እንደሚያስተናግድና በዘርፉ የዩኒቨርሲቲ ምሁራን ስልጠናው እንደሚሰጥ የገለፀው ማህበሩ በየስልጠናው መሃል እውቅ ደራሲያንና ገጣሚያን እየተገኙ ለሰልጣኞች ልምድ እንደሚያካፍሉ ለማወቅ ተችሏል፡፡ ፍላጎት ያላቸው ሰልጣኞች ከሐምሌ 1 በፊት ስቴዲየም ፊት ለፊት በሚገኘው የማህበሩ ህንፃ መጥተው እንዲመዘገቡም ጥሪ ቀርቧል፡፡
በተያያዘ ዜና ማህበሩ በየዓመቱ የሚያካሂደውን የመፅሐፍት አውደ ርዕይ ከሰኔ 24-30 ቀን 2011 ዓ.ም አራት ኪሎ ምኒልክ መሰናዶ ት/ቤት ፊት ለፊት በሚገኘው ቦታ ላይ እንደሚካሄድ ታውቋል::
ሰኔ 30 ቀን በመዝጊያው ዕለት ሰኔ 30 አገር አቀፍ የንባብ ቀን ሆኖ እንዲታወጅ እንቅስቃሴ እንደሚደረግ የተገለፀ ሲሆን ታዋቂ ሰዎች ለልጆች መፅሀፍትን እንደሚያነበኑና በፕሮግራሙ ላይ ሚኒስትሮች ታዋቂ ሰዎችና ድንገቴ እንግዳ እንደሚከሰት ለማወቅ ተችሏል፡፡

Read 10448 times