Saturday, 22 June 2019 11:11

አየር መንገድ፤ ለ3ኛ ተከታታይ ዓመት “የአፍሪካ ምርጥ” ተባለ

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(0 votes)

 የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለ3 ተከታታይ አመታት ከአፍሪካ የአንደኛነት ደረጃውን አስጠብቆ መቀጠሉ የተገለፀ ሲሆን፤ ከሰሞኑ በፈረንሳይ ፓሪስ በተከናወነ የስካይተራክስ 2019 አለማቀፍ የአየር መንገዶች ሽልማት ከአፍሪካ “ምርጥ አየር መንገድ” በመባል በ1ኛነት ደረጃ አሸንፏል፡፡ በተጨማሪም አየር መንገዱ ከአፍሪካ አየር መንገዶች ምርጥ “የቢዝነስ ክላስ” እና “ምርጥ የኢኮኖሚ ክላስ” አገልግሎት ባለቤት ነው ተብሏል፡፡ ምርጫው የተከናወነው የአየር መንገዱ ደንበኞች በሰጡት ድምጽ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን ሽልማቱን የተቀበሉት የአየር መንገዱ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ተወልደ ገ/ማርያም፣ “በደንበኞቻችን መመረጣችን አስደስቶናል፤ አገልግሎታችንንም የበለጠ እንድናሻሽል ይረዳናል” ብለዋል፡፡ በአለም ላይ 120 መዳረሻዎች ያሉት አየር መንገዱ፤ ደንበኞቹ በአገልግሎቱና በደህነነቱ ተማምነው ስለመረጡት ምስጋናም አቅርቧል፡፡ አየር መንገዱ አሁንም በአፍሪካ የመሪነቱን ቦታ ይዞ ለመቀጠል ተግቶ እንደሚሠራና የአገልግሎት ጥራቱን እንደሚያሳድግ አስታውቋል፡፡


Read 11274 times