Print this page
Monday, 01 July 2019 00:00

“ትዝብት 1” የኪነ ጥበብ ምሽት ማክሰኞ ይካሄዳል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)


    በዘንባባ የማስታወቂያ ድርጅት እና በበሊማ ኢንተርነሽናል ትሬዲንግ ትብብር የሚቀርበው “ትዝብት 1” የኪነ ጥበብ ምሽት የፊታችን ማክሰኞ ከቀኑ 11፡00 ጀምሮ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ይካሄል፡፡ በዕለቱ ጋዜጠኛ ጥበቡ በለጠ፣ ደራሲ ጌታቸው በለጠ፣ መርሻ ዮሴፍ፣ ፍቃዴ አየልኝ፣ ጋዜጠኛ ዘላለም መሉ፣ የታሪክ ምሁር ሰለሞን ተሰማ ጂ. እና ደራሲ ቆንጂት ብርሃኑ ዲስኩር የሚያቀርቡ ሲሆን ግጥም፣ ወግ፣ ሙዚቃና ጥያቄና መልስ የዝግጅቱ አካል ይሆናሉ ተብሏል፡፡
መድረኩ በደራሲ ደሳለኝ ስዩም የሚመራ ሲሆን አንጋፋው ደራሲ ክፍሉ ታደሰም በክብር እንግድነት እንደሚታደሙ ለማወቅ ተችሏል፡፡

Read 4022 times