Print this page
Saturday, 06 July 2019 13:59

በሠላሌ ዩኒቨርሲቲ የ3 ተማሪዎች ህይወት አለፈ

Written by  ሠላም ገረመው
Rate this item
(6 votes)

ፖሊስ በጉዳዩ ላይ ምርመራ እያካሄደ ነው


        በፍቼ ከተማ በሚገኘው የሠላሌ ዩኒቨርሲቲ ምንነቱ ባልታወቀ ሁኔታ የሦስት ተማሪዎች ህይወት መጥፋቱ የተገለፀ ሲሆን ፖሊስ መንስኤውን እያጣራሁ ነው ብሏል፡፡
ከአምቦ የመጣ የዩኒቨርሲቲው የሁለተኛ አመት ተማሪ የሆነው ወጣት ባጋጠመው የጤና ችግር ምክንያት ባለፈው አመት ትምህርቱን አቋርጦ በዘንድሮ አመት መቀጠሉን የጠቆሙት ምንጮች፤  ትምህርቱን ከጀመረ በኋላ ወጣቱ እራሱን ለማጥፋት በተለያዩ ጊዜያት ሙከራ አድርጎ ተማሪዎች እንዳተረፉት ይገልፃሉ፡፡
ባለፈው እሁድ ለሰኞ አጥቢያ ግን ወጣቱ ለሊት ከፎቅ ላይ ወድቆ ህይወቱ አልፎ መገኘቱን የገለፁት ምንጮች፣ አብዛኞቹ ተማሪዎች ራሱን አጥፍቶ ነው የሚል ግምት ይዘው ሠኞ እለት የመማር ማስተማሩ ሂደት በሠላም መካሄዱን ያወሳሉ፡፡
ይህ በዚህ እንዳለ ረቡዕ ጠዋት ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ ሁለት የአንደኛ አመት የእንስሳት ሳይንስ ተማሪዎች ህይወት አልፎ ተገኝቷል ያሉት ምንጮች፣ ፖሊስ ከጉዳዩ ጋር ተያያዥነት አላቸው ብሎ የጠረጠራቸውን ተማሪዎች በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያደረገ መሆኑን ገልፀዋል፡፡  

Read 8754 times