Saturday, 06 July 2019 14:17

“ሩጫና እንቅልፍ” እንዲሁም “ረበናት” ለገበያ ቀርበዋል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(1 Vote)

 በደራሲ መኮንን አረዳ የተፃፈው “ሩጫና እንቅልፍ” የተሰኘ አዲስ መፅሐፍ ሰሞኑን ለንባብ በቅቷል፡፡ በህፀፆቻችን እንድንፀፀትና በብርታታችን እንድንፀና የሚረዱ በርካታ መመሪያዎችና ምክሮች የተካተቱበት  መፅሐፉ፤አንባቢው ውስጣዊ ማንነቱን ፈትሾ ትክክለኛውን የህይወት መስመር እንዲከተል ያግዘዋል ተብሎ ይታመናል፡፡
በዚህም ምክንያት መፅሐፉ በአንዴ ተነብቦ የሚቀመጥ ሳይሆን የዕለት ተዕለት የህይወት መመሪያ ሊሆን እንደሚችል ተጠቁሟል፡፡ ደራሲው ደፈር ብሎ ያነሳቸው ትዝብቶችም፤ ለህይወት አስፈላጊና አስተማሪዎች ናቸው ተብሏል፡፡ በ200 ገጾች ተቀንብቦ፣ በ100 ብር ለገበያ የቀረበው መፅሐፉ፤ በሁሉም የመፃህፍት መደብር እንደሚገኝ ለማወቅ ተችሏል፡፡  
በተመሳሳይ፤በደራሲ ታደለ አያሌው የተደረሰው “ረበናት” የተሰኘ ልብወለድ መፅሐፍ ለንባብ በቅቷል፡፡ መፅሐፉ የስለላ ዘውግ ያለው ሲሆን መቼቱን ሰሜን ሸዋ በምትገኘው አልዩ አምባ በተባለች መንደር አዲስ አበባና ሩሲያ አድርጎ “ህብረት” የተሰኘ ተቋምና ብሔራዊ ደህንነተ የሚያደርጉትን ፍጥቫ የሚያስቃኝ ነው ተብልል፡፡ የመፅሐፉ ርዕስ የሆነው ቃል (ረበናት) ከእብራይስጥ የተወረሰ የግዕዝ ቃል ሲሆን፣ ትርጉሙም መምህራን፣ አለቆችና የመሳሰሉትን ቃላት የሚተካና ሰፋ ያለ ትርጉም እንዳለው ደራሲው ታደለ አያሌው ገልፀዋል፡፡ ደራሲው በቀጣይ በብሔራዊ ቴአትር ሊቀርብ የተዘጋጀ የሙሉ ሰዓት ቴአትር ማዘጋጀታቸውንም ጨምረው ገልፀዋል፡፡

Read 8447 times