የጋዜጠኛ ዘላለም ገበየሁ ሁለተኛ ስራ የሆነው “በገሃነም ስር መፅደቅ” የተሰኘ የግጥም መድበል ሰሞኑን ለንባብ በቅቷል፡፡
ግጥሞቹ በወቅቱ የፖለቲካ ምስቅልቅል፣ በምስቅልቅሉ ውስጥ ስላለው የተስፋ ጭላንጭል፣ የለውጡ ስጋቶችና ተስፋዎች-- ላይ የሚያጠነጥኑ ሲሆኑ መድበሉ ከ50 በላይ ግጥሞችን አካትቷል፡፡ 64 ገጾች ያሉት የግጥም መድበሉ፤በ49 ብር ከ60 ሳንቲም ለገበያ ቀርቧል፡፡ ደራሲና ጋዜጠኛ ዘላለም ገበየሁ፤ ከዚህ ቀደም “ዳሞትራ” የተሰኘ የግጥም መድበል ለንባብ ማብቃቱ አይዘነጋም፡፡