Saturday, 27 July 2019 12:02

ተገዶ መደፈር ከአእምሮ ጤና ጋር ያለው ግንኙነት

Written by  ፀሐይ ተፈረደኝ ከኢሶግ
Rate this item
(0 votes)

በአለም አቀፍ ደረጃ ወደ 15/ሚሊዮን የሚሆኑ በእድሜያቸው ከ15-19 የሆኑ ታዳጊ ልጃገረዶች በሕይወት ዘመናቸው ተገድዶ መደፈር እንደደረሰባቸው መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡
ምንም እንኩዋን በአለምአቀፍ ደረጃ መረጃዎች በትክክል ባይጠቁሙም ወንዶች ልጆች የዚህ ሰቆቃ ሰለባ እንደሚሆኑ ተጠቁሞአል፡፡
ጾታዊ ጥቃት የሚባለው በብዙ አይነት መንገድ የሚገለጽ ጥቃት ሲሆን ይኼውም ስድብን፤ ድብደባን፤ ማንቋሸሽን …ወዘተ ባጠቃላ ይም በቀጥታ በአካል ላይ ከሚደርስ ጉዳት ጀምሮ እስከ ስነልቦና ጉዳት የሚደርሱ የተለያዩ ጥቃቶች አንዱ ጾታ በሌላው ጾታ ላይ ሲያደርስ የሚገለጽ በት ነው፡፡ ነገር ግን እነዚህ ሁሉ ድርጊቶች ወደከፋ ደረጃ ሲደርሱ ወሲባዊ ጥቃትን ማለትም ጾታዊ ትንኮሳ ወይንም ጥቃት የሚያስከትሉበት አጋጣሚ ብዙ ነው፡፡ በእርግጥ ወሲባዊ ጥቃት በቀጥታ የሚነ ሳው ከሌሎቹ አይነቶች ጾታዊ ጥቃት ተከትሎ ነው ሊባል ባይችልም አንዱ ጾታ በሌላው ላይ ካለምንም ፈቃደኝነት ጉልበትን ፤ኃይልን፤ ማታለልን፤ ማባበልን…ወዘተ ተጠቅሞ በሌላው ላይ ሲፈጽመው የሰብአዊ መብትን እንደመጣስ ከሚቆጠርበት ደረጃ ይደርሳል፡፡ በማንኛውም እድሜ ያሉ ሁሉም ህጻናት ጥቃቱ ሊደርስባቸው እንደሚችል የሚገመት ሲሆን በተለይም ታዳጊዎች እንዲሁም ሴት ልጆች የጥቃቱ ሰለባ ሊሆኑ እንደሚችሉ ብዙ እውነታዎች ያሳያሉ፡፡   
እንደ ዩኒሴፍ መግለጫ በአለም አቀፍ ደረጃ የሚከተሉት መረጃዎች ተቀምጠዋል፡፡  
38 በሚሆኑ መካከለኛ ገቢ ባላቸው ሀገሮች ወደ 17/ሚሊዮን የሚሆኑ ታዳጊ ሴቶች በልጅነት እድሜያቸው ተገዶ መደፈር እንደደረሰባቸው ሪፖርት አድርገዋል፡፡ በአውሮፓ በ28 ሀገሮች ውስጥ ወደ 2.5 ሚሊዮን የሚሆኑ ታዳጊዎች ከአስራ አምስት አመት እድሜያቸው በፊት በተለያዩ መንገዶች ተገዶ መደፈር እንደደረሰባቸው የዩኒሴፍ ማስረጃ ያሳያል፡፡
በአለም አቀፍ ደረጃ ወደ 15 ሚሊዮን እድሜያቸው ከ15-19 አመት የሚሆኑ ታዳጊ ልጃገረዶች ተገዶ መደፈር የደረሰባቸው መሆኑ ሪፖርት ተደርጎአል፡፡  
በ20/ሀገሮች በተደረገ ጥናት ከአስር ታዳጊዎች ዘጠኙ እንደገለጹት ተገዶ የመደፈር ጥቃት የሚደርሰው የታዳጊነት እድሜ ሲጀምር መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ከ28 ሀገሮች የተሰበሰበ መረጃ እንደሚያሳየው ጥቃት የደረሰባቸው ልጆች ጥቃት አድራሾቹን እንደሚያውቁዋቸው ወይንም ለእነርሱ ቅርብ የሆኑ ሰዎች መሆናቸውን አስረድተዋል፡፡
ጉዋደኞች፤ በትምህርት ክፍል የሚገናኙ፤ እና የቅርብ ቤተሰቦች ታዳጊዎቹን በኃይል ለመድፈር ተጠቃሽ ከሚሆኑት መካከል መሆናቸውን በ5 ሀገራት የተደረገ ጥናት ያሳያል፡፡
በተገኘው መረጃ መሰረት በ30 ሀገራት ውስጥ ጥቃት ከደረሰባቸው ታዳጊዎች መካከል 1% የሚሆኑ ታዳጊዎች ብቻ የባለሙያ እርዳታ አግኝተዋል፡፡  
www.unicef.org June 2016
በሕጻንነት እድሜአቸው ተገዶ መደፈር የደረሰባቸው ልጆች በታዳጊነት ዘመናቸው የሚያሳዩት የተለየ ባህሪይ እና የሚደርስባቸው የአእምሮ ጭንቀት፤
በልጅነት ተገዶ የመደፈር ችግር ሲደርስ በአጭርም ይሁን በረጅም ጊዜ የሚታይ ወይንም የሚያጋጥም ችግር ተብለው ከተዘረዘሩት ውስጥ የሚከተሉት ይኝበታል፡፡
እራስን እንደጥፋተኛ መቁጠር፤ እፍረት፤ ማማረር…ወዘተ፡፡ የተፈጠረውን ተገድዶ የመደፈር ችግር ማስቆም አለመቻልን እንደ ጥፋት ቆጥሮ ማማረር በራስ ላይ የጥፋ  ተኝነት ስሜት የመሰማት ነገር ይስተዋላል፡፡ ነገር ግን መገንዘብ የሚገባው ብዙ ጊዜ ያንን ጥቃት ያደረሰን ሰው በጉልበት መክቶ ማምለጥ የማይቻል ከመሆኑ በተጨማሪ ያ አጥፊ የሆነው ሰው ሊያደርገው የሚገባውን ጥፋት ያለማድረስ ወይንም ሰውን ያለመ ጉዳት ኃላፊነት ሊሰማው እንደሚገባ እና እሱ ሊያደርገው የሚገባውን ነገር በተቃራኒው እኔ ልወጣው ይገባ ነበር ብሎ ማሰብ ትክክል አይደለም:: ምክንያቱም ያንን ለማድረግ ብዙ ጊዜ አቅም ወይንም ጉልበት ስለማይፈቅድና ድርጊቱም በድንገት የሚፈጸም በመ ሆኑ ነው፡፡
ቅርበት ወይንም ከሰዎች ጋር ግንኙነት መፍጠር፤ በልጅነቱ ተገዶ የመደፈር ጥቃት የደረሰበት በወደፊት ህይወቱ ከሰዎች ጋር የቅርብ ግንኙነት መፍጠር ወይንም እንደጉ ዋደኛ፤ወዳጅ በመሳ ሰለው መንገድ መዛመድ የማይፈልጉበት ሁኔታ ይስተዋላል፡፡ ምክ ንያቱም ቀደም ሲል በልጅነታ ቸው አስገድዶ መድፈር የፈጸመባቸውን ሰው የሚያው ቁት ወይንም የሚያምኑት አለዚያም ቤተ ሰብ ሊሆን ስለሚችል ከዚያ መጥፎ ልምድ በመነሳት የቅርብ ግንኙነታቸው ደህንነት የተሞ ላበት እና በተገደበ መልኩ እንዲሆን ይፈልጋሉ፡፡
ለራስ ዝቅተኛ ግምት መስጠት፤ በልጅነት ተገዶ የመደፈር ጥቃት የተፈጸመባቸው ለራሳቸው የሚሰ ጡት ግምት ዝቅ ያለ ይሆናል፡፡ የዚህም ምክንያቱ የደፋሪዎቹ የተበላሸ ባህርይና ድርጊት ውጤት የተደፋሪውን ስብእና መጋፋት ነው፡፡ ለራስ ዝቅተኛ ግምት መስጠት በጤና ፤በስራ፤እንዲሁም ከሰዎች ጋር የሚኖርን ግንኙነት ሊያበላሽ የሚችል ነው፡፡  
ባጠቃላይም ሕጻናት ፤ሴትም ሆነ ወንድ ተገዶ መደፈር ከደረሰባቸው በወደፊት ሕይወታቸው ላይ የሚያስከ ትለው ተጽእኖ ተመሳሳይ ነው፡፡   
ፍርሀት፤ ድብርት፤ ድርጊቱ ካለፈ በሁዋላ ሰቀቀን፤ ጭንቀት፤ ድርጊቱን ሁልጊዜ ማስታወስ፤ የአመጋገብ ስርአት ማጣት…ወዘተ የመሳሰሉት ሁሉ ይስተዋሉባቸዋል፡፡
ድርጊቱን የሚያስታውሰውን ሰውም ሆነ ቦታ ማስወገድ፤
ከወሲብ ጋር በተያያዘ ለሚነሱ ጥያቄዎች ወይንም ለሚነገሩ ነገሮች ትኩረት መስጠት፤
ተገዶ የመደፈርን መጥፎ ገጠመኝ መፍራትና በወደፊቱ ሕይወት ሰፋ ያለ ነገርን ተስፋ አለማድረግ፤
እራስን ከሰው በታች አድርጎማሰብ ወይንም ለወደፊቱም በራስ ሰውነት ላይ ቁጥጥር ለማድረግ አልችልም ብሎ ማመን፤
እራስን ለማዝናናት እንደማይችሉ መቁጠር፤ ዘና ያለ መኝታ ወይንም የእንቅልፍ ጊዜ አለመኖር፤
እራስን ከሰዎች ማግለል፤ ምንም አይነት ግንኙነት እንዳይፈጠር ማድረግ፤
ጥያቄውን ይዞ ወደፍትህ ለመቅረብ አመኔታን አጣለሁ ብሎ መስጋት፤
የመሳሰሉት በአእምሮ ላይ ከሚደርሱ ችግሮች ወይንም የጤናማነት ስሜት ማጣት ተደርገው ከሚወሰዱ መካከል ናቸው፡፡
ተገዶ መደፈር የደረሰባቸውን ሰዎች በጤናቸው ላይ ጉዳት እንዳይደርስ ለማድረግ አስቀድሞውኑ መርዳት ይቻላል፡፡
ማዳመጥ፤ ብዙ ሰዎች ችግር ሲደርስባቸው ማንም ሊያዳምጣቸው እንደማይፈልግ እና የእነ ርሱን ጉዳይ ለሌሎች ምንም አይደለም ብለው ያስባሉ ብለው ይሰጋሉ፡፡ ስለዚህ እነእርሱ የገጠ ማቸውን ነገር በግልጽ ከተናገሩ መፍትሔ ሊያገኙ እንደሚችሉና አስፈላጊ ሰዎች መሆናቸውን ማስረዳት ይገባል፡፡
የደረሰባቸውን ጥቃት ከግምት ውስጥ በማስገባት ትኩረት በመስጠት ማነጋገር…ይገባል፡፡ በእርግጥ ለማባበል እና ያልሆነ ተስፋ ለመስጠት መሞከር አይገባም፡፡ወይም ጉዳቱን እጅግ በማቃለል አይነት መቅረብ የለበትም፡፡
ልረዳህ ወይንም ልረዳሽ ዝግጁ ነኝ ማለት፡፡ ያንተ ወይንም ያንቺ ጉዳይ የእኔም ጉዳይ ነው በማለት ማነጋገር፡፡
ስለደረሰው ጉዳት ዝርዝር ማስረጃ መጠየቅ ተገቢ አይደለም፡፡ ነገር ግን ተጎጂው ሊናገር ወይንም እትንገር ከፈለገ/ች በእርጋታ ማዳመጥ ይገባል፡፡
በጊዜው ሊያገኙት የሚገባ ነገር ካለ ድጋፍ ማድረግ ይጠቅማል፡፡ ለምሳሌ ሕክምና ማግኘት፤ጉዳዩን ወደፍትህ ማድረስ የመሳሰሉትን መርዳት ተገቢ ነው፡፡
ምንጭ፡-Online.reain.org

Read 9031 times