Print this page
Saturday, 27 July 2019 12:35

እውን የኢትዮጵያ አንድነት ይመጣ ይሆን?›› መጽሐፍ ለንባብ በቃ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)


                  በደራሲ አማረ መልካ የተሰናዳው ‹‹እውን የኢትዮጵያ አንድነት ይመጣ ይሆን?›› መጽሐፍ ለንባብ በቃ፡። መጽሐፉ በዋናነት አገራችን አሁን ያለችበትን አስጨናቂ ሁኔታ ማዕከል በማድረግ በደርግና በኢሕአዴግ መንግስታት ሁኔታዎች፣ በነፃነት ምንነት በደርግና በኢህአዴግ የኢኮኖሚ ስርዓቶች፣ ከተሞቻችንና ኗሪዎቻቸው ባለፉት 27 ዓመታት በኢህአዴግ አስተዳደር ምን መልክ እንደነበራቸውና በተያያዥ ጉዳዮች ላይ የሚያነጠነጥን ሲሆን አሁን አገሪቱ ላይ ያለው ጉድለት የአገሪቱን የቀድሞ ዝናና ክብር እንዳያበላሽ ምን መደረግ አለበት በሚለውም ላይ የመፍትሄ ሀሳብን የሚያመላክት ነው፡፡
መጽሐፉ በ123 ገጽ ተመጥኖ በ75 ብር ለገበያ የቀረበ ሲሆን ደራሲው ከዚህ ቀደም ‹‹የማስተዋልና የመገንዘብ ጥረትና ውጤት›› እና ‹‹የደራሲው የሕይወት ታሪክና የወደፊት ራዕይ›› የተሰኙ መጽሐፍትን ለንባብ ማብቃታቸው ይታወሳል፡፡   


Read 642 times