Saturday, 10 August 2019 00:00

‹‹የሚያበሩ ጠሎች›› መጽሐፍ ገበያ ላይ ዋለ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

   በደራሲ ገነት ወንድሙ የተጻፈውና የአጫጭር ልቦለዶች ስብስብ የሆነው ‹‹የማያባሩ ጠሎች›› መጽሐፍ ገበያ ላይ ዋለ፡፡
መጽሐፉ በፍቅር፣ በማህበራዊ ሕይወትና ከዕለት ዕለት ሕይወት ጋር በሚገናኙ እውነታዎች ዙሪያ የሚያጠነጥኑ 16 ልቦለድ ታሪኮችን የያዘ ነው ተብሏል፡፡ ‹‹… እንደ ዋዛ የምንፈጀውን ጊዜ፣ መጀመር እንጂ መጨረስ የማንችልበትን ፍቅር ምን ያህል የመስበርና የማጉበጥ አቅም እንዳለው የገነት ብዕር ከአቅም በላይ ይነግረናል፡፡
ለምሳሌ  ‹‹ምኞትና ዕጣ››፣ ‹‹ቀን አልባ ዘመኖች››፣ ‹‹የተከፉ ጎኖች›› እና ‹‹የስዋን ወፍ›› የተሰኙትን ስራዎቿን ማየት በቂ ነው…›› በማለት ገጣሚና ደራሲ ኤፍሬም ስዩም በመጽሐፉ ጀርባ ላይ ባስቀመጠው ማስታወሻ መስክሯል በ136 ገጽ የተቀነበበው መጽሐፉ በ75 ብር ከ50 ሳንቲም ለገበያ የቀረበ ሲሆን፣ ደራሲዋ ከዚህ ቀደም ‹‹ሰንኮፍ››፣ ‹‹የዘመን ቀለማት›› እና ‹‹ከውሽንፍር ኋላ›› የተሰኙ መጽሐፍትን ለንባብ ማብቃቷ አይዘነጋም፡፡

Read 789 times