Print this page
Saturday, 10 August 2019 00:00

የብራና ግጥም በጃዝ ‹‹የት ነው የደረስነው?›› የግጥም ምሽት ሰኞ ይካሄዳል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

 በየወሩ የሚዘጋጀው ብራና ግጥም በጃዝ  የግጥም ምሽት ከነገ በስቲያ ነሐሴ 6 ቀን 2011 ዓ.ም ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ጀምሮ ‹‹የት ነው የደረስነው?›› በሚል ርዕስ ይካሄዳል፡፡
በዕለቱም በፕሮፌሰር ፍቅሬ ቶሎሳ፣ ስዩም ተሾመ፣ ዶ/ር ኤሊያስ ገብሩና ዮናስ ሀይሉ  ዲስኩር የሚቀርብ ሲሆን ገጣምያኑ ነብይ መኮንን፣ ዮሐንስ ገ/መድህንና ሰለሞን ሳህለ ትዕዛዙ ግጥም ይቀርባል፡፡
ሄኖክ ስዩምና ኮሜዲያን ፍፁም ማን አስበው (መርዞ) ወግ እንደሚያቀርቡና አልቢትር ሊደያ ታፈሰና አልቢትር ባምላክ ተሰማ በክብር እንግድነት እንደሚታደሙ፣ እንዲሁም መድረኩ በጋዜጠኛ የሸዋ ማስረሻ እንደሚመራና አጠቃላይ ዝግጅቱ በሻሎም ለኢትዮጵያ የባህል ቡድን እንደሚታጀብ የፕሮግራሙ አዘጋጅ ጉዞ ሚዲያና ማስታወቂያ ገልጿል፡፡

Read 722 times