Saturday, 10 August 2019 00:00

‹‹እግዚኦ ናዝሬት በኩለ ሌሊት አቦ አዳማ በጭለማ›› የጥበብ ምሽት ነገ በአዳማ ይካሄዳል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)


            አንጋፋውን ገጣሚ፣ ተርጓሚና ጋዜጠኛ ነብይ መኮንንን ለማወደስና ለማመስገን የታለመና በራሱ በነብይ መኮንን ‹‹እግዞ ናዝሬት በኩለ ሌሊት አቦ አዳማ በጭለማ›› በተሰኘው ግጥም መሪ ቃል የሚዘጋጅ የኪነ-ጥበብ ምሽት ነገ በአዳማ ከተማ በተስፋዬ ኦሎምፒክ ሆቴል ይካሄዳል፡፡
የሮሃ ሙዚቃል የኪነ-ጥበብ ምሽት 34ኛ ዙር በሆነው በዚህ ዝግጅት ግጥም፣ ግጥም በውዝዋዜ፣ የአንድ ሰው ተውኔትና ሌሎችም ኪነ-ጥበባዊ መሰናዶዎች እንደሚቀርቡ ከፕሮግራሙ መስራችና አዘጋጆች አንዱ የሆነው ገጣሚ ተወዛዋዥና ኬሪዮግራፈር ኤፍሬም መኮንን ገልጿል፡፡ በእለቱም ነብይ መኮንን፣ ምስራቅ ተረፈ፣ ጥላሁን ወለላው፣ ኤሊያስ ሽታሁን፣ አደም ሁሴን፣ ሰዓሊ ብሩክ ተሾመ እና ከድር አሊ ግጥም የሚያቀርቡ ሲሆን ገጣሚ ተስፋሁን ከበደና ኤፍሬም መኮንን (ኤፊማክ) ግጥም በውዝዋዜ እንዲሁም ፍራሽ አዳሹ የተሰኘ የአንድ ሰው ተውኔት በካሳሁን ከበደ እንደሚቀርብ ታውቋል፡፡
በዕለቱ ለመታደም የመግቢያ ዋጋው 50 ብር ሲሆን ሁሉም እንዲታደም አዘጋጆቹ ጋብዘዋል፡፡

Read 4328 times