Saturday, 17 August 2019 12:59

የ12ኛ ክፍል ውጤት በድጋሚ በገለልተኛ አካል እንዲጣራ ተጠየቀ

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(4 votes)

  የዘንድሮ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ውጤት፣ በድጋሚ ከሁሉም ክልሎች በተውጣጣ ገለልተኛ አካል ተጣርቶ ይፋ እንዲደረግና ስህተት በፈፀሙ አካላት ላይ የእርምት እርምጃ እንዲወሰድ የታላቋ ትግራይ ብሄራዊ ኮንግረስ (ባይቶና) ፓርቲ የጠየቀ ሲሆን የክልሉ ትምህርት ቢሮ በበኩሉ፤ በውጤቱ ላይ ያለውን ቅሬታ አቅርቧል፡፡ የኦሮሚያ ትምህርት ቢሮም ቅሬታ ማቅረቡ ታውቋል፡፡
የዘንድሮ የ12ኛ ከፍል መልቀቂያ ፈተናን ከወሰዱ ተማሪዎች መካከል ከ350 ነጥብ በላይ ያመጡት 49 ከመቶ መሆናቸውን ገልጾ ውጤቱን ይፋ ያደረገው አገር አቀፍ ፈተናዎች ኤጀንሲ፤ በዋናነት በስኮላስቲክ አፕቲቲዩድ ፈተና እርምትና ውጤት አሰጣጥ ላይ ስህተት መፈጠሩን ተገንዝቦ፣ እርምት ማድረጉን የገለፀ ሲሆን በሌሎች የትምህርት አይነት ውጤቶች ላይ ‹‹ስህተት የለም፤ ቅሬታ ያለው በግል ያቅርብ›› ብሏል፡፡
በርካታ ተማሪዎች የጠበቁትን ውጤት እንዳላገኙ በማመልከት ውጤታቸው በድጋሚ እንዲታይ ቅሬታ ማቅረባቸውንም ምንጮች ለአዲስ አድማስ የጠቆሙ ሲሆን ብሔራዊ የምዘና እና ፈተናዎች ኤጀንሲ በበኩሉ፤ ኮሚቴ አዋቅሮ ቅሬታዎችን መሠረት በማድረግ እያጣራ መሆኑን ገልጿል፡፡
የውጤት አገላለፁን ተከትሎ ቅሬታውን በይፋ ያቀረበው የትግራይ ትምህርት ቢሮ፤ ፈተናው በተሰጠበት ወቅት በአንዳንድ የአገሪቱ ክፍሎች፣ የፈተና አሰጣጥ ስነ ምግባር ጉድለት እንደነበርና ይህንንም በወቅቱ ለሚመለከተው አካል መጠቆሙን አስታውቋል፡፡
የክልሉ ትምህርት ቢሮ ሃላፊ ዶ/ር ኢንጅነር ገ/መስቀል ካህሳይ፤ ‹‹በክልላችን ፈተናው ሲካሄድ የፈተና አወሳሰድ ስነ ምግባርን ጠብቆ ነበር ይሁን እንጂ በሌሎች የአገሪቱ ክፍሎች ስርዓቱን የጠበቀ አይደለም›› ሲሉ ለመገናኛ ብዙሃን ተናግረዋል፡፡
ይህንን ቅሬታም ለትምህርት ሚኒስቴር አሳውቀው እንደነበርና ቅሬታው ምላሽ ሳይሰጠው ውጤቱ ይፋ መደረጉን ተናግረዋል:: ይሄም ኃላፊው፤ አፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጥ የትግራይ ትምህርት ቢሮ ጠይቋል።
ከወራት በፊት መሰረቱን በትግራይ አድርጎ የተቋቋመው ‹‹ባይቶና›› የተሰኘው የፖለቲካ ድርጅት ይጠይቁ›› ሲል አሳስቧል:: ‹‹ዘንድሮ የተለቀቀው የ12ኛ ክፍል ውጤት ከፍተኛ ብልሽት፣ ዝርክርክ አሰራርና የታየበት ስለሆነ ተቀባይነት የለውም፤ ውጤቱ በድጋሚ በገለልተኛ አካላት ተጣርቶ ለሕዝብ ይፋ ይደረግ ኃላፊዎችም በሕግ ይጠየቁ›› ሲል አሳስቧል፡፡      

Read 8396 times