Saturday, 17 August 2019 13:17

ሞኒካ የክሊንተንን የወሲብ ቅሌት የቲቪ ድራማ ልታደርገው ነው

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

 የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ቢል ክሊንተንን “በድብቅ አማግጠውኛል” ስትል ከ20 አመታት በፊት በአደባባይ ያጋለጠቻቸውና በወሲብ ቅሌት የአለም መነጋገሪያ ያደረገቻቸው ሞኒካ ሊውኒስኪ፤ እነሆ ሰሞኑን ደግሞ የክሊንተንን ቅሌት ከሁለት አስርት አመታት በኋላ ድራማ አድርጋ ሰርታ በቴሌቪዥን ልታሰራጨው ማሰቧን አስታውቃለች፡፡
ሞኒካ ሊውኒስኪ የታላላቅ አሜሪካውያንን የወንጀል ድርጊቶች መሰረት በማድረግ፣ የቴሌቪዥን ድራማዎችን እየሰራ ለእይታ ከሚያቀርበው ኤፍኤክስ ሾው ጋር በመተባበር የክሊንተንን የወሲብ ቅሌት “ኢምፒችመንት - አሜሪካን ክራይም ስቶሪ” በሚል ርዕስ በድራማ መልክ አዘጋጅታ በቀጣዩ አመት ለእይታ ለማብቃት እንቅስቃሴ መጀመሯን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
በመስከረም ወር 2020 በአሜሪካ ለእይታ እንደሚበቃ በሚጠበቀው የቴሌቪዥን ድራማው ላይ ሞኒካ ሊውኒስኪን ወክላ የምትጫወተው ቤኒ ፌልድስቴን የተባለች ተዋቂ የፊልም ተዋናይት እንደሆነች የጠቆመው ዘገባው፤ ቢል ክሊንተንንም ሆነ ባለቤታቸውን ሄላሪ ክሊንተንን ወክለው የሚሰሩት ተዋንያን ግን አሁንም አለመታወቃቸውን አመልክቷል፡፡
የ46 አመቷ አሜሪካዊት ሞኒካ ሊውኒስኪ፣ ከቢል ክሊንተን ጋር የፍቅር ግንኙነት በጀመረችበት ወቅት የ22 አመት ወጣት እንደነበረች ያስታወሰው ዘገባው፤ ክሊንተን በወቅቱ በ27 አመታት ያህል ይበልጧት እንደነበርም አውስቷል፡፡

Read 1885 times