Saturday, 17 August 2019 13:35

በትውልድ አይደናገር እኛም እንናገር” መጽሐፍ ላይ ነገ ውይይት ይካሄዳል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

 ሚዩዚክ ሜይዴይ ከኢትዮጵስ ኮሌጅ ጋር በመተባበር ነገ ከቀኑ 8፡00 ጀምሮ በእውቁ ፖለቲከኛ አንዳርጋቸው ጽጌ ተጽፎ በቅርቡ ለንባብ በበቃው “ትውልድ አይደናገር እኛም እንናገር” መጽሐፍ ላይ በብሔራዊ ቤተመፃሕፍትና ቤተመዛግብት ኤጀንሲ አዳራሽ ውይይት ይካሄዳል፡፡
በዕለቱ ለውይይቱ የመነሻ ሀሳብ የሚያቀርቡት የታሪክ ባለሙያና መምህር የሆኑት ቴዎድሮስ ዘርፉ ሲሆኑ መድረኩ በሰለሞን ተሰማጂ እንደሚመራ ታውቋል፡፡ ፍላጐት ያለው በውይይቱ ላይ እንዲሳተፍ ሚዩዚክ ሜይዴይ ጋብዟል፡፡

Read 2200 times