Tuesday, 20 August 2019 00:00

የአለማችን እጅግ ውዷ መኪና 18.68 ሚ. ዶላር ተሸጠች

Written by 
Rate this item
(2 votes)

  ታዋቂው የፈረንሳይ የመኪና አምራች ኩባንያ ቡጋቲ፣ እያመረታት የምትገኘውና ገና ተሰርታ ያላለቀችው ላ ቮይቸር ኖሬ የተሰኘችዋ የአለማችን እጅግ ውዷ መኪና፤ 18.68 ሚሊዮን ዶላር መሸጧን ሲኤንቢኒውስ ዘግቧል፡፡
1ሺህ 500 የፈረስ ጉልበት ያላትን ይህቺን እጅግ ዘመናዊ የቅንጦት መኪና፣ ክብረወሰን ባስመዘገበ ውድ ዋጋ የገዛው ግለሰብ ማንነት ይፋ ባይደረግም፣ አንዳንድ ውስጥ አዋቂዎች ግን የአለማችን የእግር ኳስ ኮከብ ክርስቲያኖ ሮናልዶ ሳይሆን አይቀርም ማለታቸውን ዘገባው አመልክቷል፡፡ ግለሰቡ በልዩ ሁኔታ የተመረተችዋን ብቸኛ መኪና በእጁ ለማስገባት ክፍያውን ቢፈጽምም መኪናዋን ለመረከብ ግን ሁለት አመት ከመንፈቅ ያህል ጊዜ መጠበቅ እንደሚኖርበት ኩባንያው ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡

Read 6583 times