Saturday, 24 August 2019 13:31

የአፍሪካ ቱሪዝም ኦሎምፒያድ በመጪው ጥቅምት ወር ይካሄዳል

Written by  መንግስቱ አበበ
Rate this item
(0 votes)


                በአፍሪካና በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነው የቱሪዝም ኦሎምፒያድ፣ በመጪው ጥቅምት ወር በአፍሪካ ሕብረት እንደሚካሄድ  አዘጋጆቹ አስታወቁ፡፡
ባለፈው ማክሰኞ የኦሎምፒያድ አዘጋጅ “Afri TOP” በስካይላይት ሆቴል በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ፤ ሁሉም የአፍሪካ አገራት ያላቸውን ባህላዊና ታሪካዊ እሴቶች አንድ ላይ በማድረግ ለዓለም የሚሸጡበት የቱሪዝም ገበያ ነው ብሏል፡፡
“ዋን አፍሪካ፣ ዋን ኮንቲነንት፣ ዋን ስፕሪት” በሚል መሪህ በሚዘጋጀው የቱሪዝም ኦሎምፒያድ፣ የአፍሪካ ባህላዊ እሴቶች፣ አለባበስ፣ ቅርፃ ቅርፅ የሚቀርቡ ሲሆን ሁሉም የአፍሪካ አገራት በተራ የሚያዘጋጁት ይሆናል ተብሏል፡፡
ይህን የአፍሪካ ቱሪዝም ኦሎምፒያድ ፕሮፖዛልን፤ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽ/ቤት፣ የአፍሪካ ኅብረት፣ የባህልና ቱሪዝም ሚ/ር፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርና ቱሪዝም ኢትዮጵያ አይተው ከመረመሩት በኋላ እንደተቀበሉትና ይሁንታቸውን እንደሰጡት፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርም ሁሉንም የአፍሪካ አገራት በኦሎምፒያዱ ላይ እንዲሳተፉ በይፋ መጋበዙን ለማወቅ ተችሏል፡፡

Read 767 times