Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 09 June 2012 11:35

በክ/ከተማውና በኢንሹራንስ ውዝግብ በመኪና የተገጩ ግለሰብ ህክምና አላገኙም

Written by 
Rate this item
(0 votes)

በልደታ ክ/ከተማ በቆሻሻ በሚሰበስብ መኪና ላይ በረዳትነት ለ25 አመታት የሠሩት አቶ ጉተማ አከና፤ የመኪና አደጋ ደርሶባቸው እግራቸው ክፉኛ የተጐዳ ቢሆንም እስካሁን ተገቢውን ህክምና አላገኙም ተባለ፡፡ ግለሰቡ በመ/ቤታቸው በኩል የአደጋ ኢንሹራንስ የተገባላቸው ቢሆንም እስካሁን የህክምና ገንዘቡ አልተከፈላቸውም፡፡ የ5 ልጆች አባት የሆኑት አቶ ጉተማ ባለቤታቸው የቤት እመቤት እንደሆኑና ከእጅ ወደ አፍ የሆነ ኑሮ እንደሚመሩ የአካባቢው ነዋሪዎች ገልፀዋል፡፡ ግለሰቡ ግጭቱ የደረሰባቸው ግንቦት 6 ቀን 2004 ዓ.ም ሲሆን በረዳትነት የሚሰሩበት መኪና ወደ ኋላ ተንሸራቶ አደጋውን እንዳደረሰባቸውና በተለይ የአንደኛው እግራቸው አጥንት መድቀቁን ቤተሰቦች ይናገራሉ፡፡
አደጋው እንደደረሰባቸው ወደ መንግስት ሆስፒታል ቢሄዱም አልጋ በማጣታቸው ለአራት ቀን ኮሪደር ላይ ተኝተው ጀሶ ተደርጐላቸው ይቆያሉ፡፡ ሆኖም ቁስሉ ሽታ ስላመጣና አልጋም ስላልተገኘላቸው ወደ ቤታቸው ሄደው እንዲተኙ ከሆስፒታሉ ተነገራቸውና ወደ ቤታቸው ተመለሱ፡፡ የእግራቸው ቁስልና ሽታ እየበረታ በመምጣቱ የአካባቢው ነዋሪ ገንዘብ በማዋጣት ዮርዳኖስ ሆስፒታል አስገቧቸው፡፡
የተዋጣው ገንዘብ ግን ከአልጋ ክፍያ አላለፈም፡፡ ሆስፒታሉ በእርዳታ መልክ የተወሰነ ህክምና ካደረገላቸው በኋላ ሃኪሞች ኦፕራሲዮን መደረግ እንዳለባቸው የነገሯቸው ሲሆን በተለይ አንደኛው እግራቸው አጥንቱ በመድቀቁ ወደ ጋንግሪን እንዳይቀየር መስጋታቸውን ገልፀውላቸዋል፡፡
መ/ቤታቸው ለምን እንደማያሳክማቸው ጐረቤቶች ሔደው የጠየቁ ሲሆን ያገኙት ምላሽ ግን ኢንሹራንስ አላቸው የሚል ነው፡፡ በአካባቢው ነዋሪዎች ጥያቄ የልደታ ክ/ከተማ ከኢንሹራንስ ድርጅቱ ጋር በርካታ ደብዳቤዎች ቢፃፃፍም እስካሁን የተገኘ መፍትሔ ግን የለም፡፡
መ/ቤቱ ተጐጂው እስከ 30ሺህ ብር የሚደርስ ህክምና ማግኘት እንደሚችሉ ቢገልፅም ክፍያውን መፈፀም ግን አልተቻለም፡፡ ኢንሹራንሱ ባመጣው ሁለተኛ ሃሳብ፤ መ/ቤቱ አሳክሞ ደረሰኝ ቢያመጣ እከፍላለሁ ማለቱን የሚናገሩ ቤተሰቦች፤ መ/ቤቱ ባለመስማማቱ ውዝግብ እንደተፈጠረና ግለሰቡ በህክምና እጦት ከፍተኛ አደጋ ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
አቶ ጉተማ ከዛሬ ነገ ገንዘቡ መጥቶ ኦፕራሲዮን ይደረጋሉ ተብለው እየጠበቁ ሲሆን፤ በየዕለቱ ብሩ መጥቶ ኦፕራሲዮን እደረጋለሁ በሚል ተስፋ ምግብ ሳይበሉ እንደሚውሉ ለማወቅ ተችሏል፡፡በአቶ ጉተማ ላይ አደጋ ያደረሰው የመ/ቤቱ ሹፌርም በወንጀል አለመጠየቁን ነዋሪዎቹ ይናገራሉ፡፡

Read 23245 times Last modified on Saturday, 09 June 2012 12:02