Saturday, 16 June 2012 08:51

በ30ኛው ኦሎምፒያድ የኢትዮጵያ ተስፋዎች

Written by  ግሩም ሠይፉ
Rate this item
(0 votes)

 

በለንደኑ 30ኛው ኦሎምፒያድ ኢትዮጵያ በኦሎምፒክ የተሳትፎ ታሪኳ ከፍተኛውን ውጤት
ልታስመዘግብ የምትችልበት ተስፋ ተፈጠረ፡፡ ከወር በፊት ስፖርት አድማስ ከኢትዮጵያ የኦሎምፒክ
ኮሚቴ ኤግዚኪዊቲቭ ዲያሬክተር አቶ ታምራት በቀለ ጋር ባደረገው ውይይት በለንደን ኦሎምፒክ
ለኢትዮጵያ ስንት ሜዳልያ እንጠብቅ  የሚል ጥያቄ ተነስቶ ነበር፡፡ አቶ ታምራት ሲናገሩ ብሄራዊ
ኦሎምፒክ ኮሚቴው 12 ሜዳልያዎች (4 ወርቅ፣ 4 ብር፣ 4 ነሐስ) ለመሰብሰብ በይፋ ማቀዱን
ሲናገሩ አገሪቱ ከተያዘው እቅድ በላቀ ስኬት ተጨማሪ ሜዳልያዎችን የመሰብሰብ ተስፋ እንዳላት
ገልውልን ነበር፡፡ በለንደን የሚስተናገደው 30ኛው ኦሎምፒያድ ከመጀመሩ 100 ቀናት በፊት ደግሞ
በመላው ዓለም በተለያዩ የመገናኛ ብዙሀናት እና የስፖርት ባለሙያዎች የተሰሩ ትንበያዎችን
በማጥናት በስፖርት አድማስ በተዘጋጀው ዘገባ ደግሞ ለኢትዮጵያ በአጠቃላይ 7 ሜዳልያ ከዚያ
ውስጥም 1 ወርቅ ብቻ በወንዶች 10ሺ እንደሚጠበቅ መተንበዩን በመግለጽ በኦሎምፒኩ ለኢትዮጵያ
የሜዳልያ ድል ዝቅተኛ ግምት መሰጠቱም ተዘግቦ ነበር፡፡ ካለፉት 2 ወራት ወዲህ ግን በዓለም አቀፍ
ደረጃ በተደረጉ ውድድሮች ላይ ለሚኒማቸው በተሳተፉ ኢትዮጵያዊያን የታየው ልዩ ብቃት ግን
አስቀድሞ ሲሰጥ የቆየውን ዝቅተኛ ግምት ፉርሽ እየሆነ መምጣቱ ተስተውሏል፡፡ በአውሮፓና በሰሜን
አሜሪካ በተካሄዱ የዳይመንድ ሊግ ውድድሮች በለንደን ኦሎምፒክ የሚያሳትፋቸውን ሚኒማ
ለማምጣት ኢትዮጵያውያኑ ሲሳተፉ በውጤታማነት ፍፁም የበላይነት በማሳየታቸው ለለንደን
ኦሎምፒክ ከፍተኛ የውጤት ተስፋን ለኢትዮጵያ የፈጠረ ሆኗል፡፡ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች
በመካከለኛና በረዥም ርቀት እያሳዩ የሚገኙት ድል አድራጊነትና ያላቸው ወቅታዊ ብቃት በለንደን
ኦሎምፒክ አገራችን ለምትጠብቀው ውጤት ከፍተኛ መነቃቃት ፈጥሯል፡፡ ኢትዮጵያውያኑ አትሌቶች
ለኦሎምፒኩ ከ2 ወር ያነሰ ጊዜ ሲቀር በመካከለኛ በረዥም ርቀትና በማራቶን ውድድሮች በሁለቱም
ፆታዎች ለቀረቡት የሜዳልያ ድሎች ዋንኛ ተቀናቃኝ ሆነው በመጠቀስ ላይ ናቸው፡፡ የቅርብ
ተቀናቃኞቻቸው የኬንያ፣ የኤርትራ፣ የእንግሊዝና የአሜሪካ አትሌቶች ይህን ያልተጠበቀ ሁኔታ
በከፍተኛ ስጋትና ጭንቀት በመከታተል ዝግጅታቸውን እያጧጧፉ ናቸው፡፡
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን በኦፊሴላዊ ድረገፁ እንዳቀረበው መረጃ ከሆነ ለለንደን ኦሎምፒክ
የሚዘጋጀው የኢትዮጵያ ኦሎምፒያኖች ቡድን በሁለተኛ የዝግጅት ምእራፍ ውስጥ ገብቷል፡፡
የኦሎምፒክ ዝግጅቶችና ልምምዶች በአዲስ አበባና ወጣ ባሉ የከተማዋ አካባቢዎች እየተከናወኑ
ናቸው፡፡ የ3,000 እና የ1,500 ሜትር አትሌቶች የጫካ ልምምድ እንዲሁም የ5,000 እና
10,000ሜትር አትሌቶች በአዲስ አበባ ስቴድየም ተገኝተው የማገገሚያ ስልጠና ሲከታተሉ
ሰንብተዋል፡፡ ባለፈው ሰሞን የማራቶን ቡድኑ  የመተጣጠፍና የጥንካሬ ልምምዶችን ሲሰራ መቆየቱን
የሚገልፀው የድረገፁ መረጃ በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽንና በኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ
አማካይነት አንድ ዘመናዊ ቶዮታ ሚኒ ባስ /D4D/ እና አንድ ቶዮታ ፒክ አፕ ተሸከርካሪዎች ተመድቦ
የልምምድ ጊዜያቸውን በቀን ከአንድ ጊዜ ወደ ሁለት ጊዜ በማሳደግ ጠንካራ ዝግጅት በመደረግ ላይ
መሆኑን  አስታውቋል::   በአጠቃላይ በተከታታይ የስልጠናና ልምምድ ቀናት የታየው የአትሌቶቹ
የጊዜ አጠቃቀም፣ ስልጠናን የመቀበል ብቃት፣ የቡድን ስሜትና መተሳሰብ ሁሉ ከምንጊዜውም በላይ
አኩሪ መሆኑን ፌዴሬሽኑ ይገልፃል፡፡ በ30ኛው የለንደን ኦሎምፒያድ ኢትዮጵያን የሚወክሉ
ኦሎምፒያኖች ምርጫ ከ10 ቀናት በኋላ ይፋ እንደሚሆን ይጠበቃል፡፡
በለንደኑ 30ኛው ኦሎምፒያድ ኢትዮጵያ በኦሎምፒክ የተሳትፎ ታሪኳ ትልቁን የሜዳልያ ስኬት
ልትሰበስብ እንደምትችል በልበ ሙሉነት ተስፋ ማድረግ ይቻላል፡፡
ከለንደን በፊት ኢትዮጵያ በ11 ኦሎምፒኮች በነበሯት ተሳትፎዎች 38 ሜዳልያዎች ተገኝተዋል፡፡
እነዚህ 38 ሜዳልያዎች 13 የወርቅ፣ 6 የብር እንዲሁም 10 የነሐስ ሲሆኑ በዋናነት በ3 የውድድር
አይነቶች ማለትም በ10ሺና በ5ሺ እንዲሁም በማራቶን በሁለቱም ፆታዎች ተሳታፊ በነበሩ ጀግና
የኢትዮጵያ ኦሎመፒያኖች የተሰበሰቡ ናቸው፡፡ በሌላ በኩል በኢትዮጵያ የ11 ኦሎምፒኮች የተሳትፎ
ታሪክ ከፍተኛው የሜዳልያዎች ድል የተመዘገበው በ2000 እ.ኤ.አ በአውስትራሊያ ሲድኒ በተዘጋጀው
27ኛው ኦሎምፒያድ ነበር፡፡ በሲድኒ ኦሎምፒክ የኢትዮጵያ ኦሎምፒያኖች 8 ሜዳሊያዎች (4 የወርቅ፣
2 የብርና 2 የነሐስ) ሜዳልያዎችን አግኝተዋል፡፡ በለንደን ኦሎምፒክ ከ2 ኦሎምፒኮች በፊት
የተመዘገበው ይህ ከፍተኛ የውጤት ክብረወሰን በተለያዩ ምክንያቶች ሊሻሻል እንደሚችል ተስፋ
ይደረጋል፡፡
በመካከለኛ ርቀት
በመካከለኛ ርቀት ኢትዮጵያ ዓለምአቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁና ወጣት አትሌቶችን በሁለቱም ፆታዎች
ማሠማራቷ የለንደን ኦሎምፒክ ስኬትን በአዲስ ተስፋ ያጠናከረ ነው፡፡ እነዚህ የመካከለኛ ርቀት
የዓለም ምርጥ አትሌቶች በተለይ በ800 እና የ1500 ሜትር ውድድሮች  የኢትዮጵያ አዳዲስ
የሜዳልያ ተስፋ ያጠናከሩ ኦሎምፒያኖች ሆነው በዓለም አቀፍ ደረጃ በተካሄዱ የዳይመንድ ሊግ
ውድድሮች ብቅ ብለዋል፡፡ ኢትዮጵያ በኦሎምፒክ የተሳትፎ ታሪኳ በመካከለኛ ርቀት እንደ ዘንድሮው
የለንደን ኦሎምፒክ ለሜዳልያ የቀረበችበት ጊዜ አለመኖሩ ለሚጠበቀው ከፍተኛ ውጤት  የሚጠቀስ
ታላቅ ስኬት ነው፡፡ በመካከለኛ ርቀት በ800 እና በ1500 ሜትር ውድድሮች ለንደን ላይ የሚወዳደሩ
የኢትዮጵያ ኦሎምፒያኖች በታሪክ የመጀመሪያቸው የሚሆኑ የሜዳልያ ድሎችን ከወርቅ እስከ ነሐስ
ማግኘት የሚችሉበት ከፍተኛ አስተማማኝ ወቅታዊ ብቃት ይዘዋል፡፡ በ800 ሜትር በሁለቱም
ፆታዎች ሁለት የኢትዮጵያ አትሌቶች ዓለምን አስደንቀዋል፡፡ እነዚህ ሁለት አትሌቶች በዳይመንድ
ሊግ እና በሌሎች ዓለም አቀፍ ውድድሮች የዓለምና የኦሎምፒክ ሻምፒዮን ለመሆን የበቁ ታላላቅ
አትሌቶችን ማሸነፍ የቻሉ ናቸው፡፡  ሁለቱ የ20 ዓመት ወጣት አትሌቶች በ800 ሜትር የኢትዮጵያን
ሪኮርድ በሁለቱም ፆታዎች ሊያስመዘግቡ የቻሉት ፋንቱ ማጊሶ እና መሐመድ አማን ናቸው፡፡
በዳይመንድ ሊግ የመጀመሪያው ውድድሮች በአጨራረሷ ድክመት ከአንድም ሁለቴ አሸናፊነቷን
የተነጠቀችው ፋንቱ ማጊሶ ፈጣን የብቃት መሻሻል አሳይታ ባለፉት ሁለት ተከታታይ የዳይመንድ ሊግ
ውድድሮች በድንቅ የአጨራረስ ብቃት ተመልሳለች፡፡ በ800 ሜትር የዘንድሮውን ዳይመንድ ሊግ
ውድድርን የምትመራው ፋንቱ በለንደን ኦሎምፒክ በርቀቱ ለሚቀርበው የወርቅ ሜዳልያም ቅድሚያ
ግምቱን ወስዳለች፡፡
ለዚህ ግምት ማስረጃ የሚሆነው በውድድር ዘመኑ ፋንቱ ማጊሶ ዘንድሮ ባደረገቻቸው የ800 ሜትር
ታላላቅ የሚባሉትን የደቡብ አፍሪካዋን ካስተር ሴማንያ፣ የራሽያዋን ማርያ ሳቪኖሻ እና የኬንያዋን
ፓሚላ ጄሊሞ ማሸነፍ መቻሏ ነው፡፡ በ800 ሜትር ወንዶች ደግሞ ምንም እንኳን በለንደን
ኦሎምፒክ ለሚቀርበው የወርቅ ሜዳልያ የመጀመሪያውን ግምት  በርቀቱ የዓለምን ሪኮርድ የያዘው፤
የዓለምና የኦሎምፒክ ሻምፒዮኑ ኬንያዊ አትሌት ዴቪድ ሩድሻ ቢወስድም ዋና ተቀናቃኙ
ኢትዮጵያዊው ኦሎምፒያን መሐመድ አማን ሊሆን እንደሚችል እየተጠቀሰ ነው፡፡ የሱዳኑ አቡበከር
ካኪና የአሜሪካው ኒክ ሳይመንስም በተፎካካሪነት ግምት ይኖራቸዋል፡፡ የ20 ዓመቱ መሐመድ አማን
በርቀቱ ታሪክ ድንቅ ተፎካካሪነት ካሳዩ አትሌቶች አንዱ እየተባለ ሲሆን በለንደን ኦሎምፒክ ከ3
ሜዳልያዎች ለአንዱ ያለው ዕድል ሰፊ ነው፡፡
በ1500 ሜትር ውድድር በለንደን ኦሎምፒክ ለኢትዮጵያ የሜዳልያ ዕድል ከፍተኛ ተስፋ የሚኖረው
ከወንዶች ይልቅ በሴት ኦሎምፒያኖች ነው፡፡  ለዚህም ዋናው ምክንያት በዳይመንድ ሊግ ውድድሮች
በከፍተኛ ብቃት እያሸነፉ ያሉት ሁለቱ እንስት ኦሎምፒያኖች ቃልኪዳን ገዛሐኝ እና ገንዘቤ ዲባባ
ናቸው፡፡ በአንዳንድ የስፖርት ተንታኞች አስተያየት ምናልባትም በለንደን ኦሎምፒክ በ1500 ሜትር
ለሚቀርበው የወርቅ ሜዳልያ  የኢትዮጵያ ኦሎምፒያኖች የሚኖራቸው የእርስ በራስ ፉክክር ዋናው
ትኩረት ሊሆን ይችላል፡፡ በዚሁ ርቀት ኢትዮጵያን ወክለው ለወንዶች ምድብ በሚሰለፉት የኢትዮጵያ
ኦሎምያኖች ብዙ ተስፋ ለማድረግ ቢከብድም አማን ሞቴ እና መኮንን ገ/መድህን ይጠቀሳሉ፡፡
በ3ሺ መሰናክል  በሁለቱም ፆታዎች የኢትዮጵያ ኦሎምፒያኖች ከፍተኛ የውጤት ብልጫ ካላቸው
የኬንያ እና የሩስያ አትሌቶች ጋር ከባድ ፈተና በለንደን ኦሎምፒክ ይገጥማቸዋል፡፡ ምናልባትም
የኢትዮጵያ ሴት ኦሎምፒያኖች ከወንዶቹ በተሻለ የፉክክር ደረጃ በ3ሺ መሰናክል ለኢትዮጵያ
የሜዳልያ ድል ሊያስመዘግቡ ይችላሉ፡
በማራቶን
በማራቶን ቡድን የተያዙ የኢትዮጵያን ኦሎምፒያኖች ጠንካራ ስብስብ  የተያዘበት ነው፡፡ በውድድር
ዘመኑ የማራቶን ፈጣን ሰዓቶችን ያስመዘገቡ፣ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የተካሄዱ ትልልቅ
ማራቶኖችን ያሸነፉ አዳዲስ ወጣት አትሌቶች በኢትዮጵያ የኦሎምፒክ ቡድን ይገኛሉ፡፡ ኢትዮጵያን
በኦሎምፒክ መድረክ ገናና ያደረጋት የውድድር ዓይነት ማራቶን ነው፡፡ ይሁንና በማራቶን  በቤጂንግ
ኦሎምፒክ ፀጋዬ ከበደ ካገኘው የነሐስ ሜዳልያ በፊት በ1996 እ.ኤ.አ አትላንታ ላይ በፋጡማ ሮባ
በ2000 እ.ኤ.አ ደግሞ በሲድኒ ኦሎምፒክ ገዛሐኝ አበራ የተመዘገቡት የወርቅ ሜዳልያ ድሎች ብቻ
ናቸው፡፡  ስለሆነም በኦሎምፒክ መድረክ ያላትን ደማቅ ታሪክ በተለይ ማራቶን ልዕልቷ ብላ
በዘመረችበት የውድድር መስክ ኢትዮጵያ ዘንድሮ በለንደን ኦሎምፒክ የነበራትን ክብር መመለስ
እንደምትችል ይታመናል፡፡
በኢትዮጵያ የለንደን ኦሎምፒክ የማራቶን ቡድን በወንዶች የዱባይ ማራቶንን ሲያሸንፍ በታሪክ
4ኛው ፈጣን ሰዓት ሆኖ የተመዘገበ ሰዓትን የያዘው የ21 ዓመቱ አየለ አብሽሮን ጨምሮ በዱባይና
በሮተርዳም ማራቶኖች ሁለተኛ ደረጃ ያላቸውን ዲኖ ሰፈርና ጌቱ ፈለቀን ይዟል፡፡ በሴቶች ደግሞ
የሮተርዳም ማራቶንን ያሸነፈችው ቲኪ ገላና፤ የዱባይ ማራቶንን ያሸነፈችው አሰለፈች መርጊያ እና
ማሬ ዲባባ ይገኛሉ፡፡
በ10ሺ እና በ5ሺ
በቤጂንግ ኦሎምፒክ በ10ሺና በ5ሺ ሜትር ድርብ የወርቅ ሜዳልያ በማስመዝገብ ወርቃማ ታሪክ
የሰራቸው ጥሩነሽ ዲባባ ከ2 ዓመት የጉዳት ቆይታ በኋላ ለለንደን ኦሎምፒክ በሙሉ ብቃት መመለሷ
ለኢትዮጵያ የኦሎምፒክ ሜዳልያ ስኬት መጠናከር ከፍተኛ ተስፋን ያሳደረ 3ኛው ምክንያት ነው፡፡
ከ2 ሳምንት በፊት በአሜካ ግዛቶች በተደረጉ የሚኒማ ውድድሮች ላይ በ10ሺ ሜትርና በ5ሺ ሜትር
የዓመቱን ፈጣን ሰዓቶች ያስመዘገበችው አትሌት ጥሩነሽ ዲባባ ለንደን ላይ የኢትዮጵያን የሜዳልያ
ክብር ለማስጠበቅ መቻሏ የማይቀር መሆኑንም መረጃዎች እያመለከቱ ናቸው፡፡ በ10ሺ ሜትር ሴቶች
የኦሎምፒክ ሻምፒዮኗ ጥሩነሽ ዲባባ እና በላይነሽ ኦልጀራ የኢትዮጵያን የሜዳልያ ተስፋ ሲያለመልሙ
ከቅርብ ተቀናቃኞቻቸው በዋናነነት የምትጠቀሰው የዓለም ሻምፒዮኗ ኬንያዊ አትሌት ቪቪያን
ቼሮይት ናት፡፡
በወንዶች 10ሺ ሜ የኢትዮጵያ ኦሎምፒያኖች በሄንግሎ በተካሄደ ውድድር ሚኒማ ባመጡ አትሌቶች
የተዋቀረ ነው፡፡ በ10ሺ ሜትር የቀነኒሣ በቀለ መኖር የኢትዮጵያን ቡድን በልምድ የሚያጠናክረው
ሲሆን በሄንግሎ ሚኒማቸውን ለማምጣት የቻሉት ታናሽ ወንድሙ ታሪኩ በቀለ አና ፈይሳ ሌሊሣ
በለንደን ኦሎምፒክ ጠንካራ ተፎካካሪ መሆናቸው ይጠበቃል፡፡ ለኢትዮጵያ በቅርብ ተቀናቃኝነት
የሚጠበቁት የኬንያ አትሌቶች ኪፕሮፕና ማሳይ ናቸው፡፡ በለንደን ኦሎምፒክ በ10ሺ ሜትር ወንዶች
የሁለቱን ወንድማማቾች ቀነኒሣ እና ታሪኩ በቀለ ፍጥጫ ማጋጠሙም ትኩረት ይስባል፡፡ በወንዶች
5ሺ ሜትር በለንደን ኦሎምፒክ ላይ ከፍተኛው ግምት ለእንግሊዙ አትሌት ሞፋራህ እንደተሰጠ
ነው፡፡ በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ አሜሪካዊው በርናንድ ላጋት ተጠብቋል፡፡ የኢትዮጵያ ኦሎምፒያኖች
የሜዳልያ እድል በተለይ  በወንዶች 5ሺ ሜትር  የጠበበ ዕድል ቢኖርም በዳይመንድ ሊግ ውድድር
ድንቅ ብቃት ያሳየው ደጀን ገብረመስቀልና  በሜዳልያው ፉክክር ሊገባ እንደሚችል ተስፋ
ይደረጋል፡፡ በ5ሺ ሜትር ሴቶች ለኢትዮጵያ ኦሎምፒያኖች በሜዳልያ ያለው እድል ከወንዶቹ የሚልቅ
ይመስላል፡፡ በተለይ ለወርቅ ሜዳልያውም ድል ቀዳሚው ግምት ለዓለም ሻምፒዮኗ ኬንያዊ ቪቪያን
ቼሮይት ቢሰጥም በርቀቱ ከፍተኛ ልምድ ያላት አትሌት መሠረት ደፋርና በዳይመንድ ሊግ
ያሸበረቀችው አበባ አረጋዊ ለኢትዮጵያ የተሰጠውን  ዝቅተኛ ግምት ፉርሽ ለማድረግ የሚችሉበትን
ታሪክ መስራታቸው ይጠበቃል፡፡
በለንደን ታድያ ምን ይጠበቅ?
በአጠቃላይ በ30ኛው ኦሎምፒያድ 34 ኢትዮጵያውያን ኦሎምፒያኖች በ6 የአትሌቲክስ ውድድሮች
በ2ቱም ፆታዎች ተሳታፊ ይሆናሉ፡፡ በ800 ሜ፣ በ1500ሜ፣ በ5ሺሜ፣ በ10ሺ ሜ፣ በ3ሺ መሰናክል፣
በማራቶን ውድድሮች በሁለቱን ፆታዎች በሚደረጉ ውድድሮች በድምሩ 36 የወርቅ፤ የብርና የነሐስ
ሜዳልያዎች ለሽልማት ይቀርባሉ፡፡
የኢትዮጵያ ኦሎምፒያኖች ከእነዚህ ሜዳልያዎች ሲሶ ያህሉን ሊወስዱ እንደሚችሉ በከፍተኛ ደረጃ
ተስፋ ማድረግ ይቻላል፡፡ ምናልባትም ከእነዚህ 12 ሜዳልያዎች 7ቱ ወርቅ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ሰባቱ
ወርቆች በ800 ሜትር በሁለቱም ፆታዎች፤ በ1500 ሜትር ሴቶች፤ በማራቶን በተለይ በወንዶች፤
በ10ሺ ሜትር በሁለቱም ፆታዎች ሊገኙ የሚችሉ ናቸው፡፡

 

በለንደኑ 30ኛው ኦሎምፒያድ ኢትዮጵያ በኦሎምፒክ የተሳትፎ ታሪኳ ከፍተኛውን ውጤት ልታስመዘግብ የምትችልበት ተስፋ ተፈጠረ፡፡ ከወር በፊት ስፖርት አድማስ ከኢትዮጵያ የኦሎምፒክ ኮሚቴ ኤግዚኪዊቲቭ ዲያሬክተር አቶ ታምራት በቀለ ጋር ባደረገው ውይይት በለንደን ኦሎምፒክ ለኢትዮጵያ ስንት ሜዳልያ እንጠብቅ  የሚል ጥያቄ ተነስቶ ነበር፡፡ አቶ ታምራት ሲናገሩ ብሄራዊ ኦሎምፒክ ኮሚቴው 12 ሜዳልያዎች (4 ወርቅ፣ 4 ብር፣ 4 ነሐስ) ለመሰብሰብ በይፋ ማቀዱን ሲናገሩ አገሪቱ ከተያዘው እቅድ በላቀ ስኬት ተጨማሪ ሜዳልያዎችን የመሰብሰብ ተስፋ እንዳላት ገልውልን ነበር፡፡ በለንደን የሚስተናገደው 30ኛው ኦሎምፒያድ ከመጀመሩ 100 ቀናት በፊት ደግሞ  በመላው ዓለም በተለያዩ የመገናኛ ብዙሀናት እና የስፖርት ባለሙያዎች የተሰሩ ትንበያዎችን በማጥናት በስፖርት አድማስ በተዘጋጀው ዘገባ ደግሞ ለኢትዮጵያ በአጠቃላይ 7 ሜዳልያ ከዚያ ውስጥም 1 ወርቅ ብቻ በወንዶች 10ሺ እንደሚጠበቅ መተንበዩን በመግለጽ በኦሎምፒኩ ለኢትዮጵያ የሜዳልያ ድል ዝቅተኛ ግምት መሰጠቱም ተዘግቦ ነበር፡፡

ካለፉት 2 ወራት ወዲህ ግን በዓለም አቀፍ ደረጃ በተደረጉ ውድድሮች ላይ ለሚኒማቸው በተሳተፉ ኢትዮጵያዊያን የታየው ልዩ ብቃት ግን አስቀድሞ ሲሰጥ የቆየውን ዝቅተኛ ግምት ፉርሽ እየሆነ መምጣቱ ተስተውሏል፡፡ በአውሮፓና በሰሜን አሜሪካ በተካሄዱ የዳይመንድ ሊግ ውድድሮች በለንደን ኦሎምፒክ የሚያሳትፋቸውን ሚኒማ ለማምጣት ኢትዮጵያውያኑ ሲሳተፉ በውጤታማነት ፍፁም የበላይነት በማሳየታቸው ለለንደን ኦሎምፒክ ከፍተኛ የውጤት ተስፋን ለኢትዮጵያ የፈጠረ ሆኗል፡፡ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በመካከለኛና በረዥም ርቀት እያሳዩ የሚገኙት ድል አድራጊነትና ያላቸው ወቅታዊ ብቃት በለንደን ኦሎምፒክ አገራችን ለምትጠብቀው ውጤት ከፍተኛ መነቃቃት ፈጥሯል፡፡ ኢትዮጵያውያኑ አትሌቶች ለኦሎምፒኩ ከ2 ወር ያነሰ ጊዜ ሲቀር በመካከለኛ በረዥም ርቀትና በማራቶን ውድድሮች በሁለቱም ፆታዎች ለቀረቡት የሜዳልያ ድሎች ዋንኛ ተቀናቃኝ ሆነው በመጠቀስ ላይ ናቸው፡፡ የቅርብ ተቀናቃኞቻቸው የኬንያ፣ የኤርትራ፣ የእንግሊዝና የአሜሪካ አትሌቶች ይህን ያልተጠበቀ ሁኔታ በከፍተኛ ስጋትና ጭንቀት በመከታተል ዝግጅታቸውን እያጧጧፉ ናቸው፡፡

 

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን በኦፊሴላዊ ድረገፁ እንዳቀረበው መረጃ ከሆነ ለለንደን ኦሎምፒክ የሚዘጋጀው የኢትዮጵያ ኦሎምፒያኖች ቡድን በሁለተኛ የዝግጅት ምእራፍ ውስጥ ገብቷል፡፡ የኦሎምፒክ ዝግጅቶችና ልምምዶች በአዲስ አበባና ወጣ ባሉ የከተማዋ አካባቢዎች እየተከናወኑ ናቸው፡፡ የ3,000 እና የ1,500 ሜትር አትሌቶች የጫካ ልምምድ እንዲሁም የ5,000 እና 10,000ሜትር አትሌቶች በአዲስ አበባ ስቴድየም ተገኝተው የማገገሚያ ስልጠና ሲከታተሉ ሰንብተዋል፡፡ ባለፈው ሰሞን የማራቶን ቡድኑ  የመተጣጠፍና የጥንካሬ ልምምዶችን ሲሰራ መቆየቱን የሚገልፀው የድረገፁ መረጃ በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽንና በኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ አማካይነት አንድ ዘመናዊ ቶዮታ ሚኒ ባስ /D4D/ እና አንድ ቶዮታ ፒክ አፕ ተሸከርካሪዎች ተመድቦ የልምምድ ጊዜያቸውን በቀን ከአንድ ጊዜ ወደ ሁለት ጊዜ በማሳደግ ጠንካራ ዝግጅት በመደረግ ላይ  መሆኑን  አስታውቋል::   በአጠቃላይ በተከታታይ የስልጠናና ልምምድ ቀናት የታየው የአትሌቶቹ የጊዜ አጠቃቀም፣ ስልጠናን የመቀበል ብቃት፣ የቡድን ስሜትና መተሳሰብ ሁሉ ከምንጊዜውም በላይ አኩሪ መሆኑን ፌዴሬሽኑ ይገልፃል፡፡ በ30ኛው የለንደን ኦሎምፒያድ ኢትዮጵያን የሚወክሉ ኦሎምፒያኖች ምርጫ ከ10 ቀናት በኋላ ይፋ እንደሚሆን ይጠበቃል፡፡ለንደኑ 30ኛው ኦሎምፒያድ ኢትዮጵያ በኦሎምፒክ የተሳትፎ ታሪኳ ትልቁን የሜዳልያ ስኬት ልትሰበስብ እንደምትችል በልበ ሙሉነት ተስፋ ማድረግ ይቻላል፡፡ ከለንደን በፊት ኢትዮጵያ በ11 ኦሎምፒኮች በነበሯት ተሳትፎዎች 38 ሜዳልያዎች ተገኝተዋል፡፡ እነዚህ 38 ሜዳልያዎች 13 የወርቅ፣ 6 የብር እንዲሁም 10 የነሐስ ሲሆኑ በዋናነት በ3 የውድድር አይነቶች ማለትም በ10ሺና በ5ሺ እንዲሁም በማራቶን በሁለቱም ፆታዎች ተሳታፊ በነበሩ ጀግና የኢትዮጵያ ኦሎመፒያኖች የተሰበሰቡ ናቸው፡፡ በሌላ በኩል በኢትዮጵያ የ11 ኦሎምፒኮች የተሳትፎ ታሪክ ከፍተኛው የሜዳልያዎች ድል የተመዘገበው በ2000 እ.ኤ.አ በአውስትራሊያ ሲድኒ በተዘጋጀው 27ኛው ኦሎምፒያድ ነበር፡፡ በሲድኒ ኦሎምፒክ የኢትዮጵያ ኦሎምፒያኖች 8 ሜዳሊያዎች (4 የወርቅ፣ 2 የብርና 2 የነሐስ) ሜዳልያዎችን አግኝተዋል፡፡ በለንደን ኦሎምፒክ ከ2 ኦሎምፒኮች በፊት የተመዘገበው ይህ ከፍተኛ የውጤት ክብረወሰን በተለያዩ ምክንያቶች ሊሻሻል እንደሚችል ተስፋ ይደረጋል፡፡ በመካከለኛ ርቀት በመካከለኛ ርቀት ኢትዮጵያ ዓለምአቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁና ወጣት አትሌቶችን በሁለቱም ፆታዎች ማሠማራቷ የለንደን ኦሎምፒክ ስኬትን በአዲስ ተስፋ ያጠናከረ ነው፡፡ እነዚህ የመካከለኛ ርቀት የዓለም ምርጥ አትሌቶች በተለይ በ800 እና የ1500 ሜትር ውድድሮች  የኢትዮጵያ አዳዲስ የሜዳልያ ተስፋ ያጠናከሩ ኦሎምፒያኖች ሆነው በዓለም አቀፍ ደረጃ በተካሄዱ የዳይመንድ ሊግ ውድድሮች ብቅ ብለዋል፡፡ ኢትዮጵያ በኦሎምፒክ የተሳትፎ ታሪኳ በመካከለኛ ርቀት እንደ ዘንድሮው የለንደን ኦሎምፒክ ለሜዳልያ የቀረበችበት ጊዜ አለመኖሩ ለሚጠበቀው ከፍተኛ ውጤት  የሚጠቀስ ታላቅ ስኬት ነው፡፡ በመካከለኛ ርቀት በ800 እና በ1500 ሜትር ውድድሮች ለንደን ላይ የሚወዳደሩ የኢትዮጵያ ኦሎምፒያኖች በታሪክ የመጀመሪያቸው የሚሆኑ የሜዳልያ ድሎችን ከወርቅ እስከ ነሐስ ማግኘት የሚችሉበት ከፍተኛ አስተማማኝ ወቅታዊ ብቃት ይዘዋል፡፡ በ800 ሜትር በሁለቱም ፆታዎች ሁለት የኢትዮጵያ አትሌቶች ዓለምን አስደንቀዋል፡፡ እነዚህ ሁለት አትሌቶች በዳይመንድ ሊግ እና በሌሎች ዓለም አቀፍ ውድድሮች የዓለምና የኦሎምፒክ ሻምፒዮን ለመሆን የበቁ ታላላቅ አትሌቶችን ማሸነፍ የቻሉ ናቸው፡፡  ሁለቱ የ20 ዓመት ወጣት አትሌቶች በ800 ሜትር የኢትዮጵያን ሪኮርድ በሁለቱም ፆታዎች ሊያስመዘግቡ የቻሉት ፋንቱ ማጊሶ እና መሐመድ አማን ናቸው፡፡ በዳይመንድ ሊግ የመጀመሪያው ውድድሮች በአጨራረሷ ድክመት ከአንድም ሁለቴ አሸናፊነቷን የተነጠቀችው ፋንቱ ማጊሶ ፈጣን የብቃት መሻሻል አሳይታ ባለፉት ሁለት ተከታታይ የዳይመንድ ሊግ ውድድሮች በድንቅ የአጨራረስ ብቃት ተመልሳለች፡፡ በ800 ሜትር የዘንድሮውን ዳይመንድ ሊግ ውድድርን የምትመራው ፋንቱ በለንደን ኦሎምፒክ በርቀቱ ለሚቀርበው የወርቅ ሜዳልያም ቅድሚያ ግምቱን ወስዳለች፡፡ ለዚህ ግምት ማስረጃ የሚሆነው በውድድር ዘመኑ ፋንቱ ማጊሶ ዘንድሮ ባደረገቻቸው የ800 ሜትር ታላላቅ የሚባሉትን የደቡብ አፍሪካዋን ካስተር ሴማንያ፣ የራሽያዋን ማርያ ሳቪኖሻ እና የኬንያዋን ፓሚላ ጄሊሞ ማሸነፍ መቻሏ ነው፡፡ በ800 ሜትር ወንዶች ደግሞ ምንም እንኳን በለንደን ኦሎምፒክ ለሚቀርበው የወርቅ ሜዳልያ የመጀመሪያውን ግምት  በርቀቱ የዓለምን ሪኮርድ የያዘው፤ የዓለምና የኦሎምፒክ ሻምፒዮኑ ኬንያዊ አትሌት ዴቪድ ሩድሻ ቢወስድም ዋና ተቀናቃኙ ኢትዮጵያዊው ኦሎምፒያን መሐመድ አማን ሊሆን እንደሚችል እየተጠቀሰ ነው፡፡ የሱዳኑ አቡበከር ካኪና የአሜሪካው ኒክ ሳይመንስም በተፎካካሪነት ግምት ይኖራቸዋል፡፡ የ20 ዓመቱ መሐመድ አማን በርቀቱ ታሪክ ድንቅ ተፎካካሪነት ካሳዩ አትሌቶች አንዱ እየተባለ ሲሆን በለንደን ኦሎምፒክ ከ3 ሜዳልያዎች ለአንዱ ያለው ዕድል ሰፊ ነው፡፡ በ1500 ሜትር ውድድር በለንደን ኦሎምፒክ ለኢትዮጵያ የሜዳልያ ዕድል ከፍተኛ ተስፋ የሚኖረው ከወንዶች ይልቅ በሴት ኦሎምፒያኖች ነው፡፡  ለዚህም ዋናው ምክንያት በዳይመንድ ሊግ ውድድሮች በከፍተኛ ብቃት እያሸነፉ ያሉት ሁለቱ እንስት ኦሎምፒያኖች ቃልኪዳን ገዛሐኝ እና ገንዘቤ ዲባባ ናቸው፡፡ በአንዳንድ የስፖርት ተንታኞች አስተያየት ምናልባትም በለንደን ኦሎምፒክ በ1500 ሜትር ለሚቀርበው የወርቅ ሜዳልያ  የኢትዮጵያ ኦሎምፒያኖች የሚኖራቸው የእርስ በራስ ፉክክር ዋናው ትኩረት ሊሆን ይችላል፡፡ በዚሁ ርቀት ኢትዮጵያን ወክለው ለወንዶች ምድብ በሚሰለፉት የኢትዮጵያ ኦሎምያኖች ብዙ ተስፋ ለማድረግ ቢከብድም አማን ሞቴ እና መኮንን ገ/መድህን ይጠቀሳሉ፡፡ በ3ሺ መሰናክል  በሁለቱም ፆታዎች የኢትዮጵያ ኦሎምፒያኖች ከፍተኛ የውጤት ብልጫ ካላቸው የኬንያ እና የሩስያ አትሌቶች ጋር ከባድ ፈተና በለንደን ኦሎምፒክ ይገጥማቸዋል፡፡ ምናልባትም የኢትዮጵያ ሴት ኦሎምፒያኖች ከወንዶቹ በተሻለ የፉክክር ደረጃ በ3ሺ መሰናክል ለኢትዮጵያ የሜዳልያ ድል ሊያስመዘግቡ ይችላሉ፡ በማራቶን  በማራቶን ቡድን የተያዙ የኢትዮጵያን ኦሎምፒያኖች ጠንካራ ስብስብ  የተያዘበት ነው፡፡ በውድድር ዘመኑ የማራቶን ፈጣን ሰዓቶችን ያስመዘገቡ፣ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የተካሄዱ ትልልቅ ማራቶኖችን ያሸነፉ አዳዲስ ወጣት አትሌቶች በኢትዮጵያ የኦሎምፒክ ቡድን ይገኛሉ፡፡ ኢትዮጵያን በኦሎምፒክ መድረክ ገናና ያደረጋት የውድድር ዓይነት ማራቶን ነው፡፡ ይሁንና በማራቶን  በቤጂንግ ኦሎምፒክ ፀጋዬ ከበደ ካገኘው የነሐስ ሜዳልያ በፊት በ1996 እ.ኤ.አ አትላንታ ላይ በፋጡማ ሮባ በ2000 እ.ኤ.አ ደግሞ በሲድኒ ኦሎምፒክ ገዛሐኝ አበራ የተመዘገቡት የወርቅ ሜዳልያ ድሎች ብቻ ናቸው፡፡  ስለሆነም በኦሎምፒክ መድረክ ያላትን ደማቅ ታሪክ በተለይ ማራቶን ልዕልቷ ብላ በዘመረችበት የውድድር መስክ ኢትዮጵያ ዘንድሮ በለንደን ኦሎምፒክ የነበራትን ክብር መመለስ እንደምትችል ይታመናል፡፡በኢትዮጵያ የለንደን ኦሎምፒክ የማራቶን ቡድን በወንዶች የዱባይ ማራቶንን ሲያሸንፍ በታሪክ 4ኛው ፈጣን ሰዓት ሆኖ የተመዘገበ ሰዓትን የያዘው የ21 ዓመቱ አየለ አብሽሮን ጨምሮ በዱባይና በሮተርዳም ማራቶኖች ሁለተኛ ደረጃ ያላቸውን ዲኖ ሰፈርና ጌቱ ፈለቀን ይዟል፡፡ በሴቶች ደግሞ የሮተርዳም ማራቶንን ያሸነፈችው ቲኪ ገላና፤ የዱባይ ማራቶንን ያሸነፈችው አሰለፈች መርጊያ እና ማሬ ዲባባ ይገኛሉ፡፡በ10ሺ እና በ5ሺ በቤጂንግ ኦሎምፒክ በ10ሺና በ5ሺ ሜትር ድርብ የወርቅ ሜዳልያ በማስመዝገብ ወርቃማ ታሪክ የሰራቸው ጥሩነሽ ዲባባ ከ2 ዓመት የጉዳት ቆይታ በኋላ ለለንደን ኦሎምፒክ በሙሉ ብቃት መመለሷ ለኢትዮጵያ የኦሎምፒክ ሜዳልያ ስኬት መጠናከር ከፍተኛ ተስፋን ያሳደረ 3ኛው ምክንያት ነው፡፡  ከ2 ሳምንት በፊት በአሜካ ግዛቶች በተደረጉ የሚኒማ ውድድሮች ላይ በ10ሺ ሜትርና በ5ሺ ሜትር የዓመቱን ፈጣን ሰዓቶች ያስመዘገበችው አትሌት ጥሩነሽ ዲባባ ለንደን ላይየኢትዮጵያንየሜዳልያ ክብር ለማስጠበቅ መቻሏ የማይቀር መሆኑንም መረጃዎች እያመለከቱ ናቸው፡፡ በ10ሺ ሜትር ሴቶች የኦሎምፒክ ሻምፒዮኗ ጥሩነሽ ዲባባ እና በላይነሽ ኦልጀራ የኢትዮጵያን የሜዳልያ ተስፋ ሲያለመልሙ ከቅርብ ተቀናቃኞቻቸው በዋናነነት የምትጠቀሰው የዓለም ሻምፒዮኗ ኬንያዊ አትሌት ቪቪያን ቼሮይት ናት፡፡ በወንዶች 10ሺ ሜ የኢትዮጵያ ኦሎምፒያኖች በሄንግሎ በተካሄደ ውድድር ሚኒማ ባመጡ አትሌቶች የተዋቀረ ነው፡፡ በ10ሺ ሜትር የቀነኒሣ በቀለ መኖር የኢትዮጵያን ቡድን በልምድ የሚያጠናክረው ሲሆን በሄንግሎ ሚኒማቸውን ለማምጣት የቻሉት ታናሽ ወንድሙ ታሪኩ በቀለ አና ፈይሳ ሌሊሣ በለንደን ኦሎምፒክ ጠንካራ ተፎካካሪ መሆናቸው ይጠበቃል፡፡ ለኢትዮጵያ በቅርብ ተቀናቃኝነት የሚጠበቁት የኬንያ አትሌቶች ኪፕሮፕና ማሳይ ናቸው፡፡ በለንደን ኦሎምፒክ በ10ሺ ሜትር ወንዶች የሁለቱን ወንድማማቾች ቀነኒሣ እና ታሪኩ በቀለ ፍጥጫ ማጋጠሙም ትኩረት ይስባል፡፡ በወንዶች 5ሺ ሜትር በለንደን ኦሎምፒክ ላይ ከፍተኛው ግምት ለእንግሊዙ አትሌት ሞፋራህ እንደተሰጠ ነው፡፡ በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ አሜሪካዊው በርናንድ ላጋት ተጠብቋል፡፡ የኢትዮጵያ ኦሎምፒያኖች የሜዳልያ እድል በተለይ  በወንዶች 5ሺ ሜትር  የጠበበ ዕድል ቢኖርም በዳይመንድ ሊግ ውድድር ድንቅ ብቃት ያሳየው ደጀን ገብረመስቀልና  በሜዳልያው ፉክክር ሊገባ እንደሚችል ተስፋ ይደረጋል፡፡ በ5ሺ ሜትር ሴቶች ለኢትዮጵያ ኦሎምፒያኖች በሜዳልያ ያለው እድል ከወንዶቹ የሚልቅ ይመስላል፡፡ በተለይ ለወርቅ ሜዳልያውም ድል ቀዳሚው ግምት ለዓለም ሻምፒዮኗ ኬንያዊ ቪቪያንቼሮይት ቢሰጥም በርቀቱ ከፍተኛ ልምድ ያላት አትሌት መሠረት ደፋርና በዳይመንድ ሊግ ያሸበረቀችው አበባ አረጋዊ ለኢትዮጵያ የተሰጠውን  ዝቅተኛ ግምት ፉርሽ ለማድረግ የሚችሉበትን ታሪክ መስራታቸው ይጠበቃል፡፡ በለንደን ታድያ ምን ይጠበቅ?በአጠቃላይ በ30ኛው ኦሎምፒያድ 34 ኢትዮጵያውያን ኦሎምፒያኖች በ6 የአትሌቲክስ ውድድሮች በ2ቱም ፆታዎች ተሳታፊ ይሆናሉ፡፡ በ800 ሜ፣ በ1500ሜ፣ በ5ሺሜ፣ በ10ሺ ሜ፣ በ3ሺ መሰናክል፣ በማራቶን ውድድሮች በሁለቱን ፆታዎች በሚደረጉ ውድድሮች በድምሩ 36 የወርቅ፤ የብርና የነሐስ ሜዳልያዎች ለሽልማት ይቀርባሉ፡፡ የኢትዮጵያ ኦሎምፒያኖች ከእነዚህ ሜዳልያዎች ሲሶ ያህሉን ሊወስዱ እንደሚችሉ በከፍተኛ ደረጃ ተስፋ ማድረግ ይቻላል፡፡ ምናልባትም ከእነዚህ 12 ሜዳልያዎች 7ቱ ወርቅ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ሰባቱ ወርቆች በ800 ሜትር በሁለቱም ፆታዎች፤ በ1500 ሜትር ሴቶች፤ በማራቶን በተለይ በወንዶች፤ በ10ሺ ሜትር በሁለቱም ፆታዎች ሊገኙ የሚችሉ ናቸው፡፡

 

 

Read 2459 times