Print this page
Saturday, 24 August 2019 14:42

ስለ እናት ማህበር ያዘጋጀው የኪነ-ጥበብ ምሽት ይካሄዳል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

 በ1994 ዓ.ም የተመሰረተውና በርካታ ለችግር የተጋለጡ ሕጻናትን  በመደገፍና ወላጆቻቸውንም በኢኮኖሚ ራሳቸውን በማስቻል ስራ ላይ የተሰማራው ‹‹ስለ እናት ማህበር››፣  ከጎህ የኪነ ጥበብ ምሽት አዘጋጆች ጋር በመተባበር ያሰናዳው የኪነ ጥበብና የስነ ጽሑፍ ምሽት፣ የፊታችን ማክሰኞ ከቀኑ 11፡00 ጀምሮ በአዲስ አበባ ቴአትርና ባህል አዳራሽ ይካሄዳል፡፡ የስነ ጽሑፉ ምሽት የተዘጋጀበት ዋናው አላማ፣ ማህበሩ ለሚደግፋቸው ሕጻናት ተማሪዎች ትምህርት ቁሳቁስ ለማሰባሰብ መሆኑን የ‹‹ስለ እናት›› ማህበር ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ያሬድ አብዱ ተናግረዋል።
በምሽቱ ኮሜዲያን ደረጀ ሀይሌና አስረስ በቀለ፣ ገጣሚያኑ አበረ አዳሙ፣ ሰለሞን ሳህለ ትዕዛዙ፣ ትዕግስት ማሞ፣ ኢዮብ ሙሴና ኤልያስ ሽታሁን ስራዎቻቸውን የሚያቀርቡ ሲሆን፣ ‹‹ዋ ያቺ አድዋ›› ተውኔትም እንደሚቀርብ ታውቋል፡፡ በተጨማሪም ድምጻዊ ናትናኤል ፍቃዱ ያቀነቅናል ተብሏል፡፡  የመግቢያ ዋጋው 100 ብር ነው፡፡

Read 914 times