Saturday, 24 August 2019 14:46

የጌጅ ኮሌጅ የጥናትና ምርምር ጉባኤ ዛሬ ይካሄዳል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(1 Vote)

  ‹‹ለላቀ ስኬት ጥራት ባለው ትምህርት›› በሚል መሪ ቃል የሚሰራው ጌጅ ኮሌጅ፣ በየአመቱ የሚያካሂደው የጥናትና ምርምር ጉባኤ፤ ዛሬ ከጠዋቱ 3፡00 ጀምሮ በሰሜን ሆቴል እንደሚካሄድ ኮሌጁ በላከው መግለጫ አስታውቋል፡፡ በጥናትና ምርምር ጉባኤው  የሕብረተሰቡን ችግሮች መፍታት ላይ ያተኮሩ ጥናታዊ ጽሑፎችን በማዘጋጀት ሲያቀርብ የቆየው ኮሌጁ፤ ዘንድሮም ‹‹ቢዝነስ፣ ሥራ ፈጠራና ልማት በኢትዮጵያ፣ ሁነቶች፣ ተግዳሮቶችና ዕድሎች›› በሚል ርዕስ የጥናትና ምርምር ጉባኤውን ማዘጋጀቱን አስታውቋል፡፡
በኮንፈረንሱ ተመራቂ ተማሪዎች ዕውቀትና ክህሎታቸውን ለገበያ የሚሸጡበትና የስራ ዕድል የሚፈጥሩበት በስራ ዕድል ላይ ያተኮሩ ሰባት ጥናቶች የሚቀርቡ ሲሆን በጉባኤው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ የከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ፣ የሳይንስና ኢኖቬሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተወካዮችና ባለድርሻ አካላት እንደሚሳተፉም ታውቋል፡፡

Read 5391 times