ባለፈው ሰኞ በሊቢያ የባህር ዳርቻ በደረሰ አደጋ፣ 40 አፍሪካውያን ስደተኞች ለሞት መዳረጋቸውን የዘገበው ዘ ጋርዲያን፤ ባለፉት ስምንት ወራት ሜዲትራኒያን ባህርን አቋርጠው ወደ አውሮፓ አገራት ለመግባት ሲሞክሩ ለሞት የተዳረጉ ስደተኞች ቁጥር 900 መድረሱን አመልክቷል፡፡
ባለፈው ማክሰኞ በሊቢያ የባህር ዳርቻ በደረሰው የጀልባ አደጋ 60 ያህል ስደተኞች ከሞት መትረፋቸውን የጠቆመው ዘገባው፤ አብዛኞቹም የሱዳን፣ የግብጽና የሞሮኮ ዜጎች መሆናቸውን ገልጧል፡፡ ባለፈው ወር በዚያው አካባቢ በደረሰ ተመሳሳይ አደጋ፣ 150 ስደተኞች ለሞት መዳረጋቸውን ያስታወሰው ዘገባው፤ ባለፈው አመት ብቻ በሜዲትራኒያን ባህር በደረሱ አደጋዎች ከ2 ሺህ 240 በላይ አፍሪካውያን ስደተኞች የገቡበት ሳይታወቅ መቅረቱን አመልክቷል፡፡