Saturday, 31 August 2019 14:14

“አብሮነት” የኪነ ጥበብ ምሽት ማክሰኞ ይካሄዳል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(1 Vote)


      በአብርሃም ግዛው ኢንተርቴይመንትና ኢቨንት በየወሩ የሚካሄደው የኪነ ጥበብ ምሽት፤  የዚህ ወር መሰናዶ፤ “አብሮነት” በሚል መሪ ቃል የፊታችን ማክሰኞ በኢንተርኮንትኔንታል ሆቴል ከቀኑ 11፡00 ጀምሮ እንደሚካሄድ ታውቋል፡፡
በዚህ መርሃ ግብር ላይ ፕ/ር በየነ ጴጥሮስ፣ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ኦባንግ ሜቶ፣ ዶ/ር መስከረም ለቺሳ፣ መምህር ደረጀ ነጋሽ፣ ደራሲ ዘነበ ወላ፣ አርቲስት ገነት ንጋቱ፣ ደራሲ አንዷለም አባተ (የአፀደ ልጅ)፣ ደራሲ ህይወት እምሻው፣ ደራሲ እስጢፋኖስ በፍቃዱ፣ መምህርና ደራሲ ገዛኸኝ ፀጋው (PHD) እና ደራሲ ቃልኪዳን ሀይሉና ሌሎችም በመሶብ ባህላዊ ባንድ ታጅበው፣ ሥራቸውን ያቀርባሉ ተብሏል፡፡ ታዋቂ ፖለቲከኞችና አርቲስቶችም በሰላምና አንድነት ዙሪያ የሚያጠነጥን ንግግር የሚያደርጉ ሲሆን፤ የመግቢያ ዋጋው 100 ብር መሆኑም ታውቋል፡፡

Read 5966 times