Monday, 09 September 2019 11:43

የቤተሰብ እቅድ ዘዴ እ.ኤ.አ በ2020/ በኢትዮጵያ

Written by  ፀሐይ ተፈረደኝ ከኢሶግ
Rate this item
(0 votes)


  • ኢትዮጵያ በአፍሪካ ውስጥ ከፍተኛ የሆነ የልጅ መውለድ መጠን አላቸው ከሚባሉ ሀገራት ተርታ የምትመደብ ሀገር ናት፡፡
  • በኢትዮጵያ በእድሜያቸው ከ15-አመት በታች የሚባሉ ታዳጊዎችና ወጣቶች 45 % ያህል መሆናቸው ተመዝግቦአል፡፡
  • በእርግጥ በኢትዮጵያ ከፍተኛ የሆነ ቁጥር ያላቸው እነዚህ ታዳጊና ወጣቶች በአገሪቱ ኢኮኖሚና ልማት እድገት እውን እንዲሆን ለማስቻል የሚያግዙ    ጠቃሚ ኃይል ቢሆኑም ከዚህ ውጤት ለመጠቀም ግን በቅድሚያ የውልደት እና የሞት መጠንን ከከፍተኛ ቁጥር ዝቅ ወዳለ ደረጃ ማውረድ በእጅጉ አስፈላጊ መሆኑን መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡
             
ስለዚህም እነዚህ አምራች ኃይላት በስራ ላይ ሊሰማሩ የሚችሉ ከፍተኛ አቅም ያላቸው የልማት ምንጮች ሲሆኑ ሊንከባከቡዋቸው የሚችሉዋቸው ሕጻናት ቁጥር አነስ ማለቱ ደግሞ የበለጠ ልማትን እውን እንዲያደርጉ የሚያስችላቸው ይሆናል፡፡ ሰዎች ኢኮኖሚያቸው እንዲያድግ የተሻሻለ ኑሮ እንዲኖሩ ለማድረግም የሚወለዱ ልጆች ቁጥር በአቅም መሆኑ አማራጭ አይገኝለትም፡፡ ስለዚህም ኢትዮጵያ በኢኮኖሚ፤ በማህበራዊ ፕሮግራሞች እንዲሁም በጤናው፤ ትምህርቱ እና በአጠቃላይም ደህንነትን ለማረጋገጥ እንዲቻል ከፍተኛ ስራ ይጠበቅባታል፡፡
የቤተሰብ እቅድ በ2020 (FP2020) የሚለው  በአለም አቀፍ ደረጃ ትኩረት እንዲያገኝ የተደረገው በUK አለም አቀፍ የልማት ክፍል እና Bill & Melinda Gates Foundation ከተባበሩት መንግስታት UNFPA ጋር በተመባበር በአለም ላይ ያሉ ሴቶች እና ልጃገረዶች በተለይም በማደግ ላይ ባሉ ሀገራት የሚኖሩት ስለቤተሰብ እቅድ ዘዴ እውቀቱ እንዲኖራቸው መረጃ በመስጠት፤አገልግሎቱን እንዲያገኙ ማድረግ፤ መድሀኒቶቹ በትክክል እንደአስፈላጊነቱ መገኘታቸውን ማረጋገጥ፤ የሚሉትንና ለሎችንም ያልተፈለገ እርግዝና፤ የቤተሰብ ቁጥርን መወሰን፤ የልጆችን እድሜ የማራራቅ ባጠቃላይም የቤተሰብ እቅድ ዘዴን እውን ለማድረግ በለንደን እ.ኤ.አ July 11, 2012  አለምአቀፍ ስብሰባ ተካሂዶ ነበር፡፡ ይህ ስብሰባም አለምአቀፍ ፖሊሲ መንደፍ፤ የገንዘብ አቅምን በሚመለከት፤ ለአገልግሎቱ የሚያስፈልጉ ግብአቶችን ማሟ ላት፤ በአለም ደሀ በተባሉ ሀገራት ቀደም ብሎ ባለው አገልግሎት ላይ ተጨማሪ 120/ ሚሊዮን ሴቶችና ልጃገረዶች ሰብአዊ መብታቸው በሚከበርበት መንገድ  አገልግሎቱን በ2020 እንዲያገኙ ማድረግ የሚል እቅድ ነበረው፡፡ በአለም ላይ ይህ እውን ከሆነ 100- ያል ታቀዱ እርግዝናዎች እንዳይከሰቱ፤ 50-ሚሊዮን ጽንስ ማቋረጥ እንዳይኖር፤ 212‚000- ልጅ ከመ ውለድ ጋር በተያያዘ የሚከሰት የእናቶች ሞት እንዳይኖር ማድረግ እና ወደ ሶስት ሚሊዮን ጨቅላ ሕጻናት እንዳይ ሞቱ ያስችላል ተብሎ ይገመታል፡፡ ስለዚህም በአለም ላይ የተለያዩ ሃገ ራት መንግስታት በቤ ተሰብ እቅድ ዘዴ ላይ እርስ በእርስ በተመባበር ጠንከር ያለ ስራ በመስራት ላይ መሆናቸውን የአለም የጤና ድርጅት ጽሁፍ ያሳያል፡፡     
የኢትዮጵያ መንግስትም በወጣቱ የህብረተሰብ ክፍል ላይ ያተኮረ የጤና አገልግሎቱን ሰፋ ለማድረግ ከ(2016-2020) ተግባር ላይ የሚውል ብሔራዊ እቅድ የነደፈ ሲሆን ይህም እቅድ  (2016-2030) ከአለም አቀፉ የሴቶችና የህጻናት እንዲሁም የወጣቶች ጤና እቅድ ጋር መናበብ የሚችል ነው፡፡
ባለፉት ሁለት አስርት አመታት የኢትዮጵያ መንግስት የቤተሰብ እቅድ ዘዴው በአገር ደረጃ አገልግሎቱ እንዲዳረስ ለማድረግ እና የተሻሻሉ ዘዴዎችንም እውን በማድረግ ተጠቃሚዎችም እንዲበረታቱ ለማድረግ ከፍተኛ ጥረት አድርጎአል፡፡  
በኢትዮጵያ እ.ኤ.አ ከ1990ዎቹ ጀምሮ የእርግዝና መከላከያ መድሀኒት ስርጭት እ.ኤ.አ እስከ 2014 ከ4% ወደ 42% ማደጉን መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ ምንም እንኩዋን ዛሬም ፍላጎታቸው ያልተሟላ ሴቶች ይኖራሉ ተብሎ ቢገመትም የዚህ ውጤትም ህጻናት ተጠቃሚ ሆነው እንዲ ያድጉ፤እናቶችም የተወሰነ ቁጥር ያላቸው ልጆች እንዲኖራቸው እድል ፈጥሮአል፡፡ ከ1990ዎቹ ወዲህ አንዲት ሴት የምትወልደው ልጅ ቁጥር ከሰባት ወደ 4.1 ዝቅ ማለቱ እ.ኤ.አ በ2014 ታይቶአል፡፡      
የኢትዮጵያ መንግስት እና ተባባሪ ድርጅቶቹ በኢትዮጵያ የቤተሰብ እቅድ ዘዴ አገልግሎት ላይ መዋሉ ለጤናው ዘርፍ የተሻሻለ አሰራር ጠቃሚ መሆኑን ስለሚያምኑ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር  ከ(2016-2020) በመላው ሀገሪቱ ባሉ የህክምና ተቋማት በተመሳሳይ ሁኔታ አገልግሎቱን ለማ ዳረስ እንዲያስችል ተደርጎ ፕላን ተነድፎአል፡፡ ይህ የተነደፈ ፐላን ከስነ ተዋልዶ ጤና አጠባበቅ ዘዴ ጋር ጎን ለጎን እንዲሰራ ለማስቻል ጥረት የተደረገበት ነው፡፡ ይህ Costed Implementation Plan for Family Planning in Ethiopia, 2015–2020 በሚል የተዘጋጀ ፕላን በኢትዮጵያ እንዲተገበሩ የሚፈልጋቸውን የሚከተሉትን ነጥቦች እውን ለማድረግ ያግዛል፡፡
የቤተሰብ እቅድ አገልግሎት ዘዴ የሰብአዊ መብትም ባሟላ መልኩ ማሳደግ፤
የቤተሰብ እቅድ አገልግሎት ዘዴን መጠበቅ የሚያስችሉ ሳይንሳዊ ግኝቶችን ወይንም ዘዴዎችን በተሟላ መልኩ ማዳረስ፤
የቤተሰብ እቅድ ዘዴ የጤናን ሁኔታ ለማሻሻል፤መብትን ለማረጋገጥ፤እና የኢትዮጵያን ህዝብ ደህንነት ለማረጋገጥ እንዲያስችል ተደርጎ የተዘጋጀ ነው፡፡
ይህ January 2016 ይፋ የሆነው ፕላን  ዋናው እቅዱ ጠቅለል ባለ መልኩ የሚከተሉትን ይመስላሉ፡፡
የወጣቶች እና ታዳጊዎች እርግዝናን ከ12% ወደ 3% ለመቀነስ፤
የቤተሰብ እቅድ ዘዴን አገልግሎቱን እየፈለጉ ነገር ግን የማያገኙትን በእድሜያቸው ከ15-19 አመት የሚደርሱ ሴቶችን ከ20% ወደ 10 % ዝቅ ማድረግ እና በእድሜያቸው ከ20-24 የሚሆኑ ሴቶችን አገልግሎቱን አለማግኘታቸውን ከ 18% ወደ 10% ዝቅ ማድረግ፤
ዘመናዊ ያልተፈለገ እርግዝናን መከላከያ ዘዴዎችን በእድሜያቸው ከ15-19 ለሆኑ ሴቶች ከ32% ወደ 40% ከፍ ማድረግ እና እድሜያቸው ከ20-24 ለሆኑት ደግሞ ከ38% ወደ 43% ከፍ ማድረግ፤
መረጃዎችን መሰብሰብ፤ትንታኔ መስጠት እና የመከላከያዎቹን አጠቃቀም በእድሜ እና ጾታ ለይቶ የሚያሳይ እውነታን በተሻሻለ እና በማያሻማ መልኩ ማሳየት መቻልን ያካትታል፡፡
በአለም አቀፉ ጉባኤ መነሻነት ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ በ2020 ማለትም በቀጣይ አመት እንዲደረስበት ላቀደችው የቤተሰብ ምጣኔ አገልግሎት ኢትዮጵያ ምቹ ሁኔታዎችን በመፍጠሩ ረገድ ቃል የገባ ችባቸው ነጥቦች የሚከተሉት ናቸው፡፡
የቤተሰብ ምጣኔ አገልግሎትን እውን ለማድረግ የሚወሰዱ የመከላከያ መድሀኒቶችን በ55% ከፍ ማድረግና አጠቃላይ የውልደት መጠንን ወደ 3 % ዝቅ ማድረግ እንዲሁም እ.ኤ.አ በ2020- 6.2 ሚሊየን የሚሆኑ ሴቶችና ልጃገረዶች አገልግሎቱን እንዲያገኙ ማስቻል፤
ኢትዮጵያ ለቤተሰብ እቅድ አገልግሎት የሚውል በጀትን በየአመቱ መጨመር አስፈላጊ መሆኑን አምናለች፤
ያልተፈለገ እርግዝናን መከላከያ እ.ኤ.አ ከ2005 ጀምሮ በእጥፍ አድጎአል፡፡ ቢሆንም ግን የኢትዮጵያ መንግስት አገልግሎቱን የሚፈልጉ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች እንዲያገኙ ለማስቻል እና በሁሉም የጤና ተቋማት አገልግሎቱ እንዲሰጥ ሁኔታዎችን ማመቻቸት በእቅድ የተያዘ እና እ.ኤ.አ እስከ 2020 ይተገበራል ተብሎ የሚጠበቅ ነው፡፡
ለአገልግሎቱ የሚያስፈልጉ ግብአቶች በሙሉ እንዲሟሉ ማድረግ፤
የረጅም ጊዜ ያልተፈለገ እርግዝናን አጠቃቀምን ማሳወቅና አገልግሎቱንም ማስፋት፤
ለወጣቶች ሴቶች ግልጽ እና ቅርብ የሆነ አገልግሎትን መስጠት፤
መከላከያ መድሀኒቶቹ በትክክል በጤና ተቋማቱ መኖራቸውን ማረጋገጥ፤መቆጣጠር ያስፈልጋል፡፡
የዚህም ምክንያቱ አንዳንድ ጊዜ እድሜያቸው ለግብረስጋ ግንኙነት በመድረሱ ብቻ ወሲብ መፈጸምን እየፈለጉ ነገር ግን እርግዝናው ለቀጣዮቹ ሁለት አመታት እንዳይከሰት የሚፈልጉ ይኖራሉ፡፡ ከእነዚህ መካከል 645 ሚሊዮን ማለትም 74 % የሚሆኑት ወጣቶች የሚጠቀሙት ዘመናዊውን የመከላያ ዘዴ ሲሆን ቀሪዎቹ 222 ሚሊዮን የሚሆኑት ግን ዘመናዊውን የመከ ላከያ ዘዴ አገልግሎት ሊያገኙ አልቻሉም፡፡ ስለዚህ አገልግሎቱን ለማዳረስና የመከላከያ ዘዴዎ ቹን ስርጭት በሚመለከት እ.ኤ.አ በ2020 ከተፈለገበት እንዲደረስ ከፍተኛ የሆነ ርብርብ ማድረግን ይጠይቃል፡፡

Read 6785 times