Saturday, 07 September 2019 00:00

ኮሜዲያን እሸቱ ‹‹1 ዶላር›› ስታንድአፕ ኮሜዲውን ዛሬና ነገ በአለም ሲኒማ ያቀርባል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

 በአጭር ጊዜ ውስጥ ዕውቅናንና ተወዳጅነትን እያተረፈ የመጣው ወጣት ኮሜዲያን እሸቱ መለሰ ‹‹1 ዶላር›› የተሰኘ ስታንድአፕ ኮሜዲውን በድጋሚ ዛሬና ነገ ከ11፡00 ጀምሮ በዓለም ሲኒማ ያቀርባል፡፡ ‹‹1 ዶላር›› የተሰኘው ስታንድአፕ ኮሜዲውን የዛሬ ሳምንት በአዶት ሲኒማ በሁለት ክፍል ያቀረበ ሲሆን በተለይ በ11፡00 በተካሄደው ሾው ላይ አዳራሽ ሞልቶ በርካታ ሰው በመመለሱና በህዝብ ጥያቄ በድጋሚ በዓለም ሲኒማ ለማቅረብ መወሰኑን ኮሜዲያን እሸቱ ገልጿል፡፡ በዚህ ዝግጅት ላይ ለመታደም የመግቢያ ዋጋው 200 ብር መሆኑም ታውቋል፡፡


Read 766 times