Saturday, 07 September 2019 00:00

“ኑ ነገን ዛሬ እንስራ” ተጓዥ ፌስቲቫል ነገ ይጀመራል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

“ብራይት ጐንደር መልቂ ሚዲያና ፕሮሞሽን” ከአማራ ምሁራን መማክርት ጉባኤና ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጋር በመተባበር ያዘጋጀው “ኑ ነገን ዛሬ እንስራ” የተሰኘና ህፃናትና ታዳጊዎችን የማነጽ ተጓዥ ፌስቲቫል ነገ ጳጉሜ 3 ቀን 2011 ዓ.ም ከቀኑ 7፡30 ጀምሮ ጐንደር ከተማ በሚገኘው ሀይሌ ሪዞርት ይጀመራል፡፡
የአዘጋጁ ድርጅት መስራችና ሥራ አስኪያጅ አቶ ገብረማርያም ይርጋ እንደገለፀው ፌስቲቫሉ በዋናነነት የነገ አገር ተረካቢ ልጆች በመልካም ስብዕና፣ አገራቸውን በመውደድ፣ ባህላቸውን በማወቅና ለአገርና ለማህበረሰብ ነውር የሆነውን ነገር ለይተውና ተፀይፈው እንዲያድጉ የሚያስተምርና የሚያነቃቃ ነው ብሏል፡፡ ፌስቲቫሉ በመቀጠል በባህርዳር፣ በደሴ፣ ደብረ ብርሃንና በሌሎችም ከተሞች የሚጓዝ ሲሆን፣ ለህፃናቱ ተረቶችን በመጠቀም የማህበረሰቡን የህይወት ፍልስፍና፣ ርዕዮተ አለም፣ ስነ ልቦናና ባህሉን እንዲያውቁ የሚያደርጉበት መድረክ በሁሉም ቦታዎች ላይ የሚደረግ ሲሆን፤ በየመድረኩ ህፃናትና ታዳጊዎችን የተመለከቱ ጥናታዊ ጽሑፎች፣ ለልጆች አካላዊና አእምሮአዊ እድገት የሚጠቅሙ ጨዋታዎች እና በአጠቃላይ ልጆችን ለነገ ዛሬ የምናዘጋጅበት ትልቅ ፌስቲቫል እንደሚሆን አቶ ገብረማርያም ይርጋ ገልፀዋል፡፡
መግቢያ ዋጋው ግማሽ ደርዘን ደብተር ነውም ተብሏል፡፡ 

Read 802 times