Saturday, 07 September 2019 00:00

“ጳጉሜ ፌስቲቫል” ለሁለተኛ ጊዜ እየተከበረ ነው

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

 በጳጉሜ አብ ፌስቲቫል ኃ.የተወሰነ የግል ማህበር በየአመቱ የሚከበረውና ሁለተኛው ዙር “ጳጉሜ ፌስቲቫል”፤ ከአዲሱ ገበያ ከፍ ብሎ በሚገኘው ቦታኒክ ጋርደን ከትላንት አንስቶ  በተለያዩ ዝግጅቶች መከበር ጀምሯል፡፡
ከባህልና ቱሪዝም መስሪያ ቤት ጳጉሜን የፌስቲቫል ወር አድርጎ ለማክበር እውቅና ያገኘው ድርጅቱ፤ ባለፈው አመት ከአማራ፣ ከአፋርና ከኦሮሚያ በመጡ የባህል ቡድኖችና በተለያዩ ዝግጅቶች መከበር መጀመሩን የፕሮግራሙ አዘጋጅና ባለቤት አቶ ሀይለ አብ መረሳ ተናግረዋል፡፡
ከጳጉሜ 1 ጀምሮ እስከ በዓሉ ዋዜማ በሚከበረው በዚህ ፌስቲቫል፤ የሙዚቃ ኮንሰርት፣ የስዕል አውደ ርዕይ፣ የልጆች መጫወቻ፣ የምግብ ፌስቲቫል፣ የፈረስና የግመል ግልቢያና ባህላዊ ጭፈራዎች የሚደምቅ ሲሆን በዛሬው ዕለት ‹‹ሰላምን እተክላለሁ›› በሚል መርህ ከሰላም ሚኒስቴር ጋር የችግኝ ተከላና የፓናል ውይይት እንደሚካሄድ ተገልጿል፡፡
የፌስቲቫሉ መዝጊያም ታላቁ የጃዝ አባት ሙላቱ አስታጥቄ ከክልል በሚያመጣቸው የባህል ቡድኖች ታጅቦ፣ በጎዳና ላይ የጃዝ ኮንሰርት እንደሚደምቅ ተነግሯል፡፡ 

Read 655 times