Saturday, 07 September 2019 00:00

‹‹የሀበሻ ቀልዶች›› መጽሐፍ ለንባብ በቃ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(1 Vote)

በደራሲ አስፋው መኮንን የተሰናዳው ‹‹የሀበሻ ቀልዶች›› የተሰኘ መጽሐፍ ሰሞኑን ለንባብ በቃ፡፡ መጽሐፉ በአገራችን በተለያዩ አካባቢዎች
የሚነገሩና አዳዲስ የተፈጠሩ ቀልዶች የተካተቱበት ነው ተብሏል፡፡ ቀልዶቹ በኑሯችን፣ በዕለት ተዕለት ሕይወታችን የሚያጋጥሙ እንቅፋቶችና ክፍተቶች ላይ የሚሳለቁ ሲሆን ከነዚህ መካከልም፤ ‹‹አሜሪካ ሰው አልባ መንኮራኩር ሰራች›› ቢለው አንዱ፣ ሌላው ቀበል አድርጎ ‹‹ታዲያ ምን ይገርማል የእኛስ ሀገር ውሃ አልባ ቧንቧ ሰርታ የለም እንዴ?›› የሚሉትና ሌሎችም ይገኙበታል፡፡ በ174 ገጾች የተቀነበበው መጽሐፉ፤ በ120 ብር ለገበያ ቀርቧል፡፡

Read 10784 times