Saturday, 14 September 2019 10:52

ተፎካካሪ ፓርቲዎች የምርጫና ፓርቲዎች ሕጉን ለመቃወም ‹‹ድምፃችን ይሰማ›› የሚል ንቅናቄ ሊጀምሩ ነው

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(2 votes)

 የምርጫና የፖለቲካ ፓርቲዎችን ሕግ የሚቃወሙ 65 ተፎካካሪ ፓርቲዎች፣ ሕጉ በቀጣዩ ምርጫ እንዳይተገበር የሚጠይቅ ‹‹ድምጻችን ይሰማ›› የሚል ንቅናቄ ሊጀምሩ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
ሕጉን በተደጋጋሚ ሲቃወሙ የቆዩት እነዚህ አገር አቀፍና ክልላዊ ፓርቲዎች፤ ሕጉ ስራ ላይ እንዳይውል የሚጠይቅ ንቅናቄ እንደሚጀምሩ ባለፈው ማክሰኞ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቀዋል፡፡
ሕጉ የዜጎችን የመደራጀት፣ የመምረጥና የመመረጥ መብትን የሚጥስ ነው ያሉት ፓርቲዎቹ፤ ሕጉ ከስምምነታቸው ውጪ የተጨመሩ ድንጋጌዎችን ያካተተ መሆኑን የሚያስገነዝብ ‹‹ድምፃችን ይሰማ›› በሚል ንቅናቄያቸው በሕጉ ላይ ያላቸውን ተቃውሞ መንግስት፣ የዲፕሎማቲክ ማህበረሰቡና ሕዝቡ እንዲገነዘብ ለማድረግ ማለማቸውን አስረድተዋል፡፡
“በሕጉ ላይ ያለን ቅሬታ ሳይደመጥ ሕጉ በቀጣዩ ምርጫ ተግባራዊ የሚደረግ ከሆነ፣ ከምርጫው ራሳችንን እስከማግለል የሚደርስ እርምጃ እንወስዳለን” ብለዋል - ፓርቲዎቹ፡፡
በሌላ በኩል፤ በቅርቡ የፓርቲዎች የጋራ ም/ቤት፣ በሕጉ እጣ ፈንታ ላይ ያደረገው ውይይት ባለመስማማት መቋጨቱን ምንጮች ለአዲስ አድማስ ጠቁመዋል፡፡  

Read 7150 times