Saturday, 14 September 2019 11:26

ሕክምና እንዲያድግ ጥናትና ምርምር ያስፈልጋል

Written by  ፀሐይ ተፈረደኝ ከኢሶግ
Rate this item
(0 votes)

የኢትዮጵያ የማህጸንና ጽንስ ሐኪሞች ማህበር ESOG እ.ኤ.አ August 22-24/2019 በኢት ዮጵያ አቆጣጠር ነሐሴ 16-18/2011 ድረስ በአዲስ አበባ የጤና ጉዳይን በሚመለከት ጥናትና ምርምር ለሚያደርጉ የይሁንታን ፈቃድ ለመስጠት እንዴት ይቻላል በሚል ለሶስት ቀናት በአዲስ አበባ ስልጠና አካሂዶአል፡፡ ስልጠናው የተሰጠው በተለያዩ ሆስፒታሎች ለሚሰሩ የማ ህጸንና ጽንስ ሐኪሞች እና የማህበረሰብ ጤና ሳይንስ ባለሙያዎች ነው፡፡ የዚህ ስልጠና አላማና ጥቅምን በሚመለከት የኢትዮጵያ የማህጸንና ጽንስ ሐኪሞች ማህበር ቦርድ ፕሬዝደንት እና የማህጸንና ጽንስ ሕክምና እስፔሻሊስት የሆኑትን ዶ/ር ድልአየሁ በቀለን መልስ እናስነብባ ችሁዋለን፡፡
ዶ/ር ድልአየሁ ለሀሳባቸው መነሻ ያደረጉት ‹‹ሕክምና እንዲያድግ ጥናትና ምርምር ያስፈል ጋል›› የሚለውን ነው፡፡ ሁልጊዜም የህክምና አማራጮች ማለትም የትኛው ከየትኛው ይሻላል የሚለውን መለየት የሚቻለው በጥናትና ምርምር ነው፡፡ ስለሆነም ማንኛውም ጥናት የሚያደ ርግ ሰው ጥናትና ምርምር ማድረግ ሲፈልግ የጥናት ስነምግባርን በተከተለ መልኩ ምርምሩን ማካሄድ ይጠበቅበታል:: የዚህም ዋነኛ ምክንያት በጥናቱ ላይ የሚሳተፉ ሰዎች በጥናት ምክን ያት አላስፈላጊ ጉዳት እንዳይደርስባቸው ለማድረግ ስለሚጠቅም ነው፡፡ የሚደረገው ጥናትም በትክክለኛው መንገድ ተጠናቆ አስፈላጊውን ጥቅም መስጠት ስላላበት ይህን ሂደት በተገቢው ለማካሄድ የተለያዩ ተቋማት ውስጥ Institutional review board የሚባል ይቋቋማል:: ይህም ማለት ማንኛውንም ለጥናት የሚቀርብ ሀሳብ ገምግሞ ሃሳቡንና የታቀደውን አካሄድ ፈትሾ ይህ ጥናት ቢሰራ ጠቃሚ ውጤት ይኖረዋል በሚል የሚያሳልፍ ቦርድ ማለት ነው፡፡ እንደዚህ ያሉት ቦርዶች በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ወይንም የሙያ ማህበራት ሊቋቋሙ ይችላሉ፡፡ የኢትዮ ጵያ የማህጸንና ጽንስ ሐኪሞች ማህበር እስከአሁን ድረስ እንደዚህ አይነት ስራ የሚሰራ ቦርድ ያልነበረው ሲሆን አንዳንድ ጥናቶች ሲደረጉ ፕሮፖዛሎች ወደ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ወይንም ቅዱስ ጳውሎስ ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ እየተላኩ ይሁን ታን እንዲያገኙ ይጠባበቁ የነበረ ነበር፡፡ ወደፊት ግን ከማህጸንና ጽንስ ሕክምና ወይንም ከስነተዋልዶ ጤና እንዲሁም በተ ለያዩ ተያያዥ በሆኑ የጤና ሁኔታዎች ላይ ጥናትና ምርምር ለሚያደርጉ ባለሙያዎች የታ ቀደው ጥናት ጠቃሚ ነው ይቀጥል ወይንም ይሰራ የሚል የይሁንታ ፈቃድ መስጠት የሚችል Insti- tutional review board በማህበሩ ለማቋቋም እንዲቻል ታስቦ የመጀ መሪያውን ስልጠና ማድ ረግ ተችሎአል፡፡ ወደስራው ለመግባት የሚያስፈልጉ እውቀቶችና ችሎ ታዎች ስለሚያ ስፈልጉ ቀጣይ ሂደቶች እንዲሟሉና የታመነባቸው ባለሙያዎች ተመርጠው ቦርዱ እንዲቋቋም ይደረ ጋል ብለዋል ዶ/ር ድልአየሁ በቀለ፡፡   
እንደዚህ አይነት ቦርዶች እንዲቋቋሙ የሚፈቅድ አካል አለ? ለሚለው ጥያቄ ዶ/ር ድልአየሁ ሲመልሱ በአገር አቀፍ ደረጃ በሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር National ethics review board የሚባል የጥናት ስነምግባሮችን የሚያይ ቦርድ አለ፡፡ ይህ ቦርድ በአገር ጉዳይ ወይም አዳዲስ መድሀኒቶችን ሰው ላይ እንደመሞከር አይነት ከበድ ያለ ውሳኔን በሚመለከት ለጥናት የሚቀ ርቡ ፕሮፖዛሎች በዚህ ቦርድ እንዲታይ ይደረጋል፡፡ ይህ National ethics review board የሚቀ ርቡለትን ፕሮፖዛሎች ፈትሾ ይሁንታን ከመፍቀድ በተጨማሪ በየተቋማቱ ወይንም በኮሌጆች ለሚቋቋሙት Institutional review board ፈቃድ የሚሰጥ መንግስታዊ አካል ነው፡፡ ስለዚህ የኢትዮጵያ የማህጸንና ጽንስ ሐኪሞች ማህበር ይህንን የጥናት ስነምግባር ስልጠና ያዘጋጀው ከሳይንስና ቴክኖሎጂ በመጡ ባለሙያዎች አማካኝነት ሲሆን በስተመጨረሻም የቦርድ አባላቱን መርጦ ወደ ስራው ለመግባት የዚህን መስሪያ ቤት ፈቃድ ማግኘት ይጠበቅበታል፡፡
National ethics review board አምስተኛው የስራ መመሪያ እንደሚጠቁመው የሰዎችን ጤና በሚመለከት ጥናትና ምርምር ማድረግ በምድር ላይ ተግባራዊ መሆን ከጀመረ የቆየ ቢሆንም ነገር ግን በጊዜው ጥናቱ ሳይንሳዊ ያልሆነ ፤ያልተቀናጀ፤እና ቁጥጥር ያልተደረገበት የስነምግባር ጉድለት በከፍተኛ ሁኔታ የሚታይባቸው ነበሩበት፡፡ ቢሆንም ግን አንዳንድ የጥናት ውጤቶች በከፊልም ቢሆን ዛሬም ድረስ በዘመናዊው የጤና አጠባበቅ ስራ ላይ መኖራቸውን ሰነዱ ይመሰ ክራል፡፡ ከጤና ጋር በተያያዘ የነበሩት ጅምር ጥናትና ምርምሮች ምንም እንኩዋን ከስነምግባር ውጪ ነበሩ ቢባልም በተሻለ ሁኔታ አገልግሎቱን ለማዳረስ የሚደረጉ ጥናቶች በራስ ወይንም በግል ምርምር ከማድረግ ጀምሮ እንስሶችን መጠቀም እንዲሁም ሰዎች ላይ ሙከራ በማድረግ ቀስ በቀስ አስከፊው ሁኔታ እየተለወጠና አሰራሩ እያደገና እየተሸሻለ የመጣ ለመሆኑ ስራ ላይ የዋሉ የምርምር ውጤቶች ምስክሮች ናቸው ይላል መረጃው፡፡        
ዶ/ር ድልአየሁ እንደሚሉትም ቀደም ባሉት ዘመናት ስነምግባራቸውን ያልጠበቁ ብዙ የተሰሩ ጥናቶች እንደነበሩ ታሪክ ይመሰክራል፡፡ ለእንደዚህ ያለው አሰራር መነሻ የሆኑትም በተለይም በሁለተኛው የአለም ጦርት ጊዜ የናዚ ወታደሮች፤ሳይንቲስቶች፤ሐኪሞች በተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ወይንም አይሁዶች ላይ በሰው ላይ እንደላቦራቶሪ እንስሳ ስነምግባሩን ያልጠበቀ ምር ምሮች ሲሰሩባቸው ነበረ፡፡ በዚያን ጊዜ ሰው ምን ያህል ቅዝቃዜን መቋቋም ይችላል እያሉ  ሰዎችን ወደ ማቀዝቀዣ የመክተት ያህል እየተመራመሩባቸው ነበር:: የሰው ልጅ ቅዝቃዜው ስንት ሲደርስ ነው የሚሞተው? እስከስንት ድረስስ መቋቋም ይችላል? እያሉ የሚዘገንኑ ጥናቶች ይሰሩ ነበር፡፡ ከዚያም በሁዋላ አሜሪካ ውስጥ በጥቁሮች ላይ እንደ ቂጥኝ የመሳሰሉ የተከሰቱ ሕመሞች ሳይታከሙ ቢቀሩ ምን ይሆናሉ? ሰዎቹ መጨረሻቸው ምንድነው የሚል አሰቃቂ የሆነ ጥናትና ምርምር ሲካሄድ ነበር፡፡ ከዚህም በላይ ሲፒሊስ ለተባለው ሕመም መድ ሀኒቱን ለማግኘት ይፈተሸበት የነበረው ጥናትና ምርምር እጅግ ዘግናኛ ነበር፡፡ ታይፐስ የተባ ለውን በሽታ ቫይረስ በመርፌ ለጤናማዎቹ ጥቁሮች እየሰጡ እና በተለየ ክፍል ውስጥ እያስቀ መጡ የትኛው መድሀኒት በሽታውን ያድናል? የሚለውን ምርምር ያደርጉ ነበር፡፡ ከእንደዚህ ያሉት የተሳሳቱ የጥናትና ምርምር ስራዎች  በመነሳት አካሄዱ ትክክል ያልሆነ ኢሰብአዊ ድር ጊት እንዲወገድና ጥናት ማድረግ ሲያስፈልግ መመሪያ ወጥቶለት ምንም ሰው ሳይጎዳ መካሄድ አለበት እንጂ በሰዎች ላይ ግፍ መፈጸም የለበትም በሚል ስነምግባርን ወደ ተከተለ አሰራር ተገባ:: ስለዚህም በአሁኑ ወቅት በየትኛውም አገር ማንኛውም ጥናት የስነምግባር ፍተሻ ሳይደ ረግበት እና በጥናቱ የሚካተቱት ሰዎች መብት የሚከበር መሆኑ ሳይረጋገጥ አይፈቀድም፡፡
Institutional review board የሚባለውን ቦርድ ለማቋቋም፤
የሰለጠነ የሰው ኃይል (ባለሙያ) ያስፈልጋል፡፡ ስለዚህም የመጀመሪያው ደረጃ ጥናት ከተካሄደ በሁዋላ ቦርድ የሚሆኑት ባለሙያዎች ማንነት ይወሰናል፡፡
ቦርድ የሚሆኑት ባለሙያዎች ከተመረጡ በሁዋላ Standard operating procedure የሚባል  ዶክመንት ያዘጋጃሉ፡፡
ዶክመንት ከተዘጋጀ በሁዋላ እውቅናን ለማግኘት ለNational ethics review board (ለብሔራዊ የጥናት ስነምግባር ግምገማ ቡድን) ይቀር ባል፡፡
ዶ/ር ድልአየሁ በቀለ የማህጸንና ጽንስ ሕክምና እስፔሻሊስት፤ በቅዱስ ጳውሎስ ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ መምህር እና በኢትዮጵያ የማህጸንና ጽንስ ሐኪሞች ማህበር የቦርድ ፕሬዝ ዳንት በስተመጨረሻው እንዳከሉት በኢትዮጵያ የእናቶች ሞት በጣም ከፍተኛ ነው፡፡ የስነተዋልዶ ጤና ችግርም ከፍተኛ ነው፡፡ ችግር አለ ማለት ደግሞ ብዙ መፍትሔ የሚፈልጉ ነገሮች አሉ ማለት ነው፡፡  ስለዚህም የእናቶችና የህጻናቱን ጤና ለመጠበቅ እንዲሁም ሞትን ለማስቀረት ምን ቢደረግ የተሻለ መፍትሔ ያስፈልጋል ለሚለው መልሱ ብዙ ያልተደረሰበት እና መጠናት ያለበት ነገር አለ ማለት ነው:: ስለዚህም፤
በስነተዋልዶ ጤና ዙሪያ የጥናት አስፈላጊነት በጣም ሰፊ ነው፡፡ በግልጽ የሚታየውም ችግሩ ስላለ መሰራት ያለበት ብዙ ጥናት መኖሩን ነው፡፡
ሌላው በስነተዋልዶ ጤና ዙሪያ ጥናት መስራት ለሚፈልጉ ሌሎች ማለትም በሌላ ሙያ ለተሰማሩ ሰዎች በሙያው ላይ ያሉት ባለሙያዎች መምራት መንገድ ማሳየት ስለሚ ጠበቅባቸው ከጨ ቅላ ሕጻናት፤ ከእናቶች እንዲሁም ከስነተዋልዶ ጤና ጋር በተያያዘ ጥናቶች በሚደረጉበት ጊዜ ስነምግባሩን የጠበቀ እንዲሆን የኢትዮጵያ የማህጸንና ጽንስ ሐኪሞች ማህበር ድርሻውን እንዲያበረክት ያስችለዋል፡፡      

Read 8204 times