Print this page
Saturday, 21 September 2019 12:30

‹‹መስቀልና ባህላዊ አከባበር›› የመዝናኛ ፕሮግራም ይካሄዳል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(1 Vote)

 አብርሃም ግዛው ኢንተርቴይመንትና የፕሬስ ስራዎች ድርጅት ከጄቲቪ ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ‹‹መስቀልና ባህላዊ አከባበር›› በሚል ርእስ መስከረም 17 ቀን 2011 ዓ.ም ከቀኑ 10-12፡00 ሰዓት ጀምሮ በጄቲቪ ኢትዮጵያ የሚተላለፍ ልዩ የበዓል ፕሮግራም ማዘጋጀቱን አስታወቀ፡፡
በፕሮግራሙ ላይ የመስቀል በዓል ባህላዊ አከባበር፣ ጭፈራ፣ የአገር ሽማግሌዎች ምርቃት፣ የእንግዶች ተሞክሮ፣ ስታንዳፕ ኮሜዲ፣ ባህላዊ ሙዚቃና የታዋቂ ሰዎች የበዓል ተሞክሮ እንደሚቀርብ ተገልጿል፡፡ የዚህ መርሃ ግብር ቀረጻም ነገ እሁድ መስከረም 11 ቀን 2012 ዓ.ም ከቀኑ 6፡00 ጀምሮ በካፒታል ሆቴል ባህላዊ የምግብ አዳራሽ ውስጥ እንደሚከናወን የፕሮግራሙ አዘጋጅ አብርሃም ግዛው አስታውቋል፡፡

Read 8626 times