Saturday, 21 September 2019 12:35

‹‹ኢትዮጵያዊነትና ኢትዮጵያኒዝም ትግል ከፍልስፍናና ከታሪክ አንጻር›› የተሰኘ ውይይት ነገ ይካሄዳል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(2 votes)

ሚዩዚክ ሜይ ዴይ ከኢትዮጲስ ኮሌጅ ጋር በመተባበር ነገ ከቀኑ 8፡00 ጀምሮ ኢትዮጵያዊነትና ኢትዮጵያኒዝም ትግል ከፍልስፍናና ከታሪክ አንጻር…›› የተሰኘ ጥናታዊ ጽሑፍ ላይ በብሄራዊ ቤተ-መጻሕፍትና ቤተ-መዛግብት ኤጀንሲ አዳራሽ ውይይት ይካሄዳል፡፡
ለውይይቱ የመነሻ ሀሳብ የሚያቀርቡት በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ የፍልስፍናና የማህበራዊ ሳይንስ መምህር ተሾመ አበራ (ዶ/ር) ሲሆኑ መድረኩ በሰለሞን ተሰማ ጂ እንደሚመራ የገለፀው አዘጋጁ፤ ፍላጎት ያለው በውይይቱ ላይ እንዲሳተፍ ጋብዟል፡፡

Read 8672 times