ሚዩዚክ ሜይ ዴይ ከኢትዮጲስ ኮሌጅ ጋር በመተባበር ነገ ከቀኑ 8፡00 ጀምሮ ኢትዮጵያዊነትና ኢትዮጵያኒዝም ትግል ከፍልስፍናና ከታሪክ አንጻር…›› የተሰኘ ጥናታዊ ጽሑፍ ላይ በብሄራዊ ቤተ-መጻሕፍትና ቤተ-መዛግብት ኤጀንሲ አዳራሽ ውይይት ይካሄዳል፡፡
ለውይይቱ የመነሻ ሀሳብ የሚያቀርቡት በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ የፍልስፍናና የማህበራዊ ሳይንስ መምህር ተሾመ አበራ (ዶ/ር) ሲሆኑ መድረኩ በሰለሞን ተሰማ ጂ እንደሚመራ የገለፀው አዘጋጁ፤ ፍላጎት ያለው በውይይቱ ላይ እንዲሳተፍ ጋብዟል፡፡