Tuesday, 01 October 2019 10:16

8ኛው ብሌን የኪነጥበብ ምሽት ማክሰኞ ይካሄዳል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

 የኢትዮጵያ ደራሲያን ማህበር በየወሩ የሚያዘጋጀው ብሌን የኪነጥበብ ምሽት 8ኛው ዙር መርሃ ግብር “የዘመን ቀለማት” በሚል ርዕስ
የፊታችን ማክሰኞ ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ጀምሮ በብሔራዊ ቴአትር ይካሄዳል፡፡ በምሽቱ ሞሃዘ ጥበባት ዳንኤል ክብረት፣ ዶ/ር ምህረት ደበበ፣ ፀደቀ ይሁኔ (ኢ/ር)፣ ኮሜዲያን አዝመራው ሙሉሰው እንዲሁም ገጣሚያኑ አበረ አያሌው፣ ልዑል ሀይሌ፣ በቃሉ ሙሉና ማህሌት አፈወርቅ ሥራዎቻቸውን የሚያቀርቡ ሲሆን መግቢያ በነፃ መሆኑ ታውቋል፡፡

Read 6454 times