Print this page
Thursday, 03 October 2019 00:00

ከ30 ሚ. ዶላር በላይ ሃብት ያፈሩ ባለጸጎች ቁጥር 265 ሺህ 490 ደርሷል

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

ባለፈው የፈረንጆች አመት 2018 ብቻ በአለማችን ከ30 ሚሊዮን ዶላር በላይ የተጣራ ሃብት ያፈሩ 2 ሺህ 124 አዳዲስ እጅግ ባለጸጎች መፈጠራቸውንና በአለማችን የሚገኙ ከ30 ሚሊዮን ዶላር በላይ የተጣራ ሃብት ያላቸው እጅግ ባለጸጎች ቁጥር 265 ሺህ 490 መድረሱን  ዘ ጋርዲያን ዘግቧል፡፡
ዌልዝ ኤክስ የተሰኘው አለማቀፍ የጥናት ተቋም ሰሞኑን ያወጣውን አመታዊ ሪፖርት ጠቅሶ ዘገባው እንዳለው፣ በአለማችን የተለያዩ አገራት የሚኖሩት የእነዚህ 265 ሺህ 490 እጅግ ባለጸጎች ድምር ሃብት 32.3 ትሪሊዮን ዶላር ይጠጋል፡፡
ከ30 ሚሊዮን ዶላር በላይ የተጣራ ሃብት ካፈሩት ከእነዚሁ የአለማችን እጅግ ባለጸጎች መካከል 31 በመቶ ያህሉ በአሜሪካ እንደሚኖሩ የጠቆመው ሪፖርቱ፤ 9 በመቶው በቻይና፣ 7 በመቶ ያህሉ ደግሞ በጃፓን እንደሚኖሩ አመልክቷል፡፡ 8ሺህ 989 እጅግ ባለጸጎች የሚኖሩባት የአሜሪካዋ ኒው ዮርክ ከአለማችን ከተሞች መካከል ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ባለጸጎች የሚገኙባት ቀዳሚዋ ከተማ ናት ያለው ሪፖርቱ፤ ከ30 ሚሊዮን ዶላር በላይ የተጣራ ሃብት ካፈሩት የአለማችን 265 ሺህ 490 እጅግ ባለጸጎች መካከል የሴቶች ድርሻ 14.6 በመቶ ብቻ መሆኑንም ገልጧል፡፡


Read 2394 times
Administrator

Latest from Administrator