Print this page
Saturday, 05 October 2019 00:00

በሲዳማ ዞን ለደረሰው ጉዳት ካሣ ሊከፈል ነው

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(0 votes)

 ከሲዳማ የክልልነት ጥያቄ ጋር ተያይዞ በዞኑና በሀዋሳ ከተማ ከተፈጠረው ሁከት ጋር ተያይዞ ንብረታቸው ለወደመባቸው ዜጎች ካሣ ለመክፈል መዘጋጀቱን የደቡብ ክልል መንግስት አስታወቀ፡፡
በአሁኑ ወቅት በሁከቱ ንብረት የወደመባቸውንና ጉዳት የደረሰባቸውን ዜጎች የመለየትና የጉዳቱን መጠን የማስላት ተግባር እየተከናወነ መሆኑን ያመለከተው የክልሉ መንግስት፤ ለካሣ የሚከፈለው ገንዘብ ከፍተኛ መሆኑንም ጠቁሟል፡፡ ለካሣ የሚያስፈልገው ገንዘብም ባለሀብቶችንና ለጋሾችን በማስተባበር ለማሰባሰብ መታቀዱም ተገልጿል፡፡ የፖለቲካ ፓርቲዎችና የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች፣ ለተጎጂዎች ካሣ እንዲከፈል በተደጋጋሚ ሲጠይቁ መቆየታቸው  ይታወቃል::

Read 972 times