Saturday, 05 October 2019 00:00

‹‹ሀሳብ ነኝ እና ሌሎች” የግጥም መድብል ዛሬ ይመረቃል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(1 Vote)

 በገጣሚ ወጣት ማህሌት አፈወርቅ የተፃፉ የግጥም ስብስቦችን ያካተተው ‹‹ሐሳብ ነኝ› እና ሌሎችም” የግጥም መድበል ዛሬ ከቀኑ 8፡00 ጀምሮ አምስት ኪሎ በሚገኘው ቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለሥልጣን ይመረቃል፡፡
በምረቃ ሥነሥርዓቱ ላይ የተለያዩ ኪነ ጥበባዊ መሰናዶዎች የሚቀርቡ ሲሆን ደራሲ ጌታቸው በለጠ፣ ደራሲና ባለቅኔ አበረ አዳሙ፣ አርቲስት ስዩም ተፈራ፣ አርቲስት ፍቃዱ ከበደ፣ ገጣሚ ደምሰው መርሻ፣ ገጣሚ ኤፍሬም ስዩም፣ ገጣሚ ሰለሞን ሳህለ፣ ገጣሚ ትዕግስት ማሞ፣ ገጣሚ ባሳ መኩሪያና ሌሎችም ስራዎቻቸውን ያቀርባሉ ተብሏል፡፡
በ110 ገፆች የተቀነበበው መጽሐፉ፤ በ59 ብር ከ99 ሳንቲም ለገበያ ቀርቧል፡፡

Read 3528 times