Saturday, 19 October 2019 12:30

9ኛው “ለዛ” ሽልማት ሐሙስ ተካሄደ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

“ደርሶ መልስ”፣ ጐሳዬ ተስፋዬ፣ ጃምቦ ጆቴ…ተሸልመዋል

            በሸገር 102.1 ሬዲዮ የሚተላለፈው ለዛ ፕሮግራም የሚያዘጋጀው የኪነጥበብ ባለሙያዎች  ሽልማት ከትላንት በስቲያ ሐሙስ 9ኛውን የሽልማት ፕሮግራም በሒልተን ሆቴል አካሄደ፡፡
በ11 ዘርፎች የኪነጥበብ ባለሙያዎችን ሲያወዳድር የቆየው የሽልማት ድርጅቱ፤ አሸናፊዎችን ከየዘርፉ ሸልሟል፡፡ በምርጥ ፊልም “ቁራኛዬ” ፊልም፣ በምርጥ ሴት መሪ ተዋናይነትና በምርጥ ወንድ ተዋናይ ዘርፍ ሶስት ዋንጫዎችን ሲሰበስብ፣ “ደርሶ መልስ” ድራማ በምርጥ የቴሌቪዥን ተከታታይ ፊልም፣ አርቲስት ሀና ዮሐንስ በ “ዘመን” ድራማ ምርጥ ተዋናይት ዘርፍ፣ በምርጥ ነጠላ ዜማ ዘርፍ የኦሮምኛው ድምፃዊ ጃምቦ ጆቴ “በልባ” ሲሸለም በምርጥ የሙዚቃ ቪዲዮ የጐሳዬ ተስፋዬ “ከእሁድ እስከ እሁድ” ተሸልሟል፡፡ በዓመቱ ምርጥ ዘፈን ዘርፍ የበሀይሉ ታፈሰ (ዚጊዛጋ) “ሰርካለሜ”አሸናፊ ሆኗል፡፡

Read 959 times