Print this page
Saturday, 26 October 2019 11:30

‹‹ሰለሜክራሲ›› የግጥም መጽሐፍ ገበያ ላይ ዋለ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

 በገጣሚ ዳንኤል ቢሰጥ እቴቴ (ወዳችን) የተጻፉ በርካታ ግጥሞችን የያዘው ‹‹ሰለሜክራሲ›› የግጥም መድበል ገበያ ላይ ዋለ፡፡ ግጥሞቹ ፀሃፊው በተለያየ ወቅት በሕይወት መንገዱ ያያቸውን፣ የታዘባቸውንና ያነበባቸውን ሁነቶችና የፈጠሩበትን ስሜት በቃላት ሰድሮ ሃሳቡን ለመግለጽ እንደሞከረ በመግቢያው ላይ ባሰፈረው ማስታወሻ ገልጿል፡፡ በ100 ገጾች የተቀነበበው የግጥም መጽሐፉ፤ በ56 ብር ከ60 ሳንቲም ለገበያ ቀርቧል፡፡
ገጣሚና ደራሲ ዳንኤል ቢሰጥ ከዚህ ቀደም፣ ‹‹የታች ሰፈር ልጆች›› የቀልድ ስብስብ››፣ ‹‹አፈር ብላ›› የግጥም ስብስብና ‹‹ሜክሲኮ ቡናና ሻይ›› የወጎች ስብስብ መጽሐፍን ለንባብ ማብቃቱ አይዘነጋም፡፡


Read 1183 times