ትናንት ምሽት ቦሌ በሚገኘው ኩሪፍቱ ዲፕሎማት ላውንጅ በተካሄደ ስብሰባ ላይ ባለሀብቶች በፊልም ላይ መዋዕለ ንዋያቸውን አፍስሰው ተጠቃሚ በመሆን ለጥበቡ እድገት የበኩላቸውን አስተዋፅኦ እንዲያደርጉ ተጠየቁ፡፡ ስብሰባውን ያዘጋጀው በመጪው አዲስ አመት “Colours of the Nile” ዓለም አቀፍ ፊልም አውደርዕይ የሚያቀርበው ብሉናይል ፊልም እና ቴሌቪዥን አካዳሚ ሲሆን በስብሰባው ላይ ከባለሀብቶች በተጨማሪ ዓለም አቀፍ የፊልም ባለሙያዎች ተገኝተዋል፡፡