Print this page
Saturday, 26 October 2019 11:58

በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ 57 ኢትዮጵያውያን በጥቃትና ግጭት መገደላቸውን አለማቀፍ ሪፖርት አስታወቀ

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(0 votes)

    ካለፈው መስከረም አጋማሽ ጀምሮ በደቡብ ክልል ጂንካ በቦዲ ማህበረሰብ እና በፀጥታ ሃይሎች መካከል በተፈጠሩ ተከታታይ ግጭቶች 40 ያህል ሰዎች መገደላቸውን የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ ድጋፍ ማስተባበሪያ ሪፖርት አስታውቋል፡፡
በአካባቢው በሚኖሩ የቦዲ ማህበረሰብ እና በመከላከያ ሠራዊት መካከል የተፈጠረው ግጭት መነሻው ለጊቤ 3 ግድብ እና የስኳር ፕሮጀክት አካባቢው በመንግስት መፈለጉን ተከትሎ መሆኑን ሪፖርቱ አትቷል፡፡ የቦዲ ማህበረሰቦች የመንግስትን ምትክ ቦታ ሰጥቶ መልሶ ማስፈር ፕሮግራም በመቃወማቸው ግጭቱ ካለፈው መስከረም ወር ጀምሮ መከሰቱን ሪፖርቱ ይፋ አድርጓል፡፡ ይህ ግጭት ያዝ ለቀቅ እያደረገ እስካሁን 40 ያህል ሰዎች መገደላቸውን ማስተባበሪያ ጽ/ቤቱ የገለፀ ሲሆን መንግስት ለጉዳዩ አስቸኳይ እልባት እንዲያበጅለትም ጠይቋል፡፡ በዚህ ሪፖርት መሠረትም ካፈው መስከረም ወር አጋማሽ ጀምሮ በአፋር እና በደቡብ በተፈጠሩ የፀጥታ ችግሮች እና ጥቃቶች 57 ኢትዮጵያውያን መገደላቸውንና 34 ያህል መቁሰላቸውን አስታውቋል፡፡ ከእነዚህ መካከል 17 ያህሉ በቅርቡ በአፋር በታጠቁ ሃይሎች የተገደሉ መሆናቸውም ታውቋል፡፡  

Read 1179 times