Print this page
Saturday, 26 October 2019 11:58

የ‹‹ግዮን›› መጽሔት ማኔጂንግ ዳይሬክተር ታሠረ

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(1 Vote)

የሣምንታዊ ‹‹ግዮን›› መጽሔት ማኔጂንግ ዳይሬክተር ጋዜጠኛ ፍቃዱ ማህተመወርቅ ከ6 አመት በፊት በእንቁ መጽሔት ምክንያት በተከሰሰበት የግብር ጉዳይ መታሰሩ ታውቋል፡፡
ጋዜጠኛው ማክሰኞ ጥቅምት 11 ቀን 2012 ዓ.ም ከ6 አመት በፊት የ‹‹እንቁ›› መጽሔት አሣታሚ በነበረበት ወቅት በተከሰሰበት የግብር ስወራና የታክስ ጉዳይ ፍ/ቤት ቀርቦ ጥፋተኛ ነህ ተብሏል፡፡
የጥፋተኛነት ውሣኔውን ተከትሎም በእስር ቤት እንዲቆይ ሆኖ ማክሰኞ ጥቅምት 18 ቀን 2012 የቅጣት ውሣኔ እንዲቀበል ፍ/ቤቱ ብይን ማስተላለፉን ለማወቅ ተችሏል፡፡
ከጥፋተኝነት ውሣኔው በኋላ አዲስ አድማስ ያነጋገረው ጋዜጠኛ ፍቃዱ ማህተመወርቅ፤ በሀገሪቱ ለውጥ መምጣቱን ተከትሎ በተስፋ ለመስራት ያቋቋመው ‹‹ግዮን›› መጽሔት በእስሩ ምክንያት መቋረጡን አስታውቋል፡፡

Read 8451 times