Print this page
Saturday, 26 October 2019 12:01

ኢትዮጵያዊው ሠለሞን አየለ የ‹‹ሂውማን ራይትስ ዎች›› የአፍሪካ ተጠሪ ሆነው ተሾሙ

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(5 votes)

አለማቀፉ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅት ‹‹ሂውማን ራይትስ ዎች›› ኢትዮጵያዊውን ሠለሞን አየለ ደርሶ የአፍሪካ ዋና ተጠሪ አድርጐ መሾሙን አስታወቀ፡፡
ከትናንት በስቲያ 33ኛ መደበኛ ጉባኤውን ያደረገው ‹‹ሂውማን ራይትስ ዎች›› በህግና በዲሞክራሲያዊ መብቶች አጠባበቅ የዳበረ ልምድና እውቀት አላቸው ያላቸውን አቶ ሠለሞን አየለን የአፍሪካ ዋና ተጠሪ አድርጐ መርጧል፡፡
አቶ ሠለሞን አየለ ደርሶ በአፍሪካ በህግና በዲሞክራሲ ኤክስፐርትነትና አማካሪነት ሰፊ ልምድ እንዳላቸውም ተገልጿል፡፡ በአፍሪካ ያለውን የሰብአዊ መብት አጠባበቅ በተሻለ ሁኔታ ይከታተላሉ ተብሎም ተስፋ ተጥሎባቸዋል፡፡
በአለማቀፍ ህግ ፕሮፌሰር የሆኑት የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንኮ ተወላጁ ሬሜ ኒጐያ ሊሙባን ደግሞ የ‹‹ሂውማን ራይትስ ዎች ም/ኮሚሽነር ሆነው መሾማቸው ታውቋል፡፡
ሁለቱ ተሿሚዎች በአፍሪካ ያለውን የሠብአዊ መብት አያያዝና አጠባበቅ ይከታተሉ ማሻሻያ እንዲያደርግም ያግዛሉ ተብሎ ተስፋ እንደተጣለባቸው ታውቋል፡፡
‹‹ሂውማን ራይትስ ዎች›› ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት ላይ በተደጋጋሚ በሚያወጣቸው ሪፖርቶች ጠንካራ ትችት የሚሰነዘር መሆኑም ይታወቃል፡፡
ከዚህ ቀደም የአሁኑ የኢትዮጵያ ሠብአዊ መብት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ የሂውማን ራይትስዎች የምስራቅ አፍሪካ ተጠሪ ሆነው ተሾመው እንደነበር ይታወሳል፡፡  

Read 8801 times