Saturday, 02 November 2019 13:44

ማን ምን አሰ? (በወቅታዊ ቀውስ ዙሪያ)

Written by 
Rate this item
(0 votes)


- “…በእርግጥ ኢትዮጵያዊ ትስስሩ ጠንካራ ስለሆነ የአንድነታችን ገመድ አልበጠስ ብሎ ነው እንጂ፣ ክስተቱ አንድነታችንን ለመበጠስ የተሰራ ነው…”
    አቶ ሙሉጌታ አበበ (የመኢአድ ም/ሊቀ መንበር)
- “…ይሄኔ ሌላ አገር ቢሆን ግልብጥብጥ የሚልበት ሁኔታ ይፈጠር ነበር፡፡ መከራን ተሸክሞ ነገን በተስፋ ማየት ባህላችን ነው፡፡…”
    አቶ ይልቃል ጌትነት (የኢህን ሊቀ መንበር)
• “…ከዚህ እንቅስቃሴ ፖለቲካዊ ትርፍ አገኛለሁ የሚል አካል ካለ እርካሽ ነው:: አገር እየፈረሰ ፖለቲካዊ ትርፍ አገኛለሁ ማለት ሞኝነት ነው፡፡…”
   አቶ ሙሉጌታ አበበ (የመኢአድ ም/ሊቀመንበር)
• “…እኛ እንደ ድርጅት ከኢትዮጵያ ሰላምና አንድነት በላይ ምንም የሚመለከተን ነገር የለም፡፡ ይህ ነገር የሥልጣን ወይም ማን የበላይነት ይያዝ የሚል ጉዳይ አይደለም:: ይህ ጉዳይ አገርን የማዳንና በሰላም ወደሚቀጥለው ምዕራፍ ማሸጋገር ነው:: በዚህ ጉዳይ ላይ ከመንግስት ጋር በምንም መልኩ እንተባበራለን፡፡…”
   ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነገ (የኢዜማ መሪ)
• “…የአገር መሪ በመሪነት ተግባሩ ላይ፣ ፖሊስ በፖሊስ ሥራው፣ ደህንነቱ በተመደበበት ሥራ፣ ጦር ሠራዊቱ በአገር ጥበቃ ሥራ፣ ሁሉም በተሰማራበት
ተግባር ላይ ኃላፊነቱን ካልተወጣ ሥራው ምንድን ነው?...”
     ሙፍቲ ሐጂ ዑመር እድሪስ (የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠ/ምክር ቤት ፕሬዚዳንትና የጉባኤው የበላይ ጠባቂ)


Read 1478 times