- የሻማዎቹ ዋጋ ከኬኩ ዋጋ ከበለጠ፣ ዕድሜህ መግፋቱን ትገነዘባለህ፡፡
ቦብ ሆፕ
- አዛውንቶች ሁሉን ነገር ያምናሉ፤ መካከለኛ ዕድሜ ላይ ያሉቱ ሁሉን ነገር ይጠረጥራሉ፤ ወጣቶች ሁሉን ነገር ያውቃሉ፡፡
ኦስካር ዋይልድ
- ሰው ለመተኛት አልጋ ላይ ከመውጣቱ በፊት ቁጣውን ወይም ንዴቱን መርሳት አለበት፡፡
ሞሃንዳስ ጋንዲ
- አንዳንድ ሰዎች የቱንም ያህል ቢያረጁ፣ ውበታቸው አ ይነጥፍም - ከ ፊታቸው ወ ደ ልባቸው ይሻገራል እንጂ፡፡
ማርቲን ቡክስባዩም
- ለህፃናት ሁሌም መልካም ሁን፤ የመጨረሻ ማረፊያ ቤትህን የሚመርጡልህ እነሱ ናቸውና፡፡
ፊሊስ ዲለር
- የሞት ፍራቻ የሚመነጨው ህይወትን ከመፍራት ነው፡፡ ህይወቱን በተሟላ መልኩ የሚመራ ሰው በማንኛውም ጊዜ ለመሞት ዝግጁ ነው፡፡
ራልፍ ዋልዶ ኢመርሰን
- ከትላንት ተማር፤ ዛሬን ኑርበት፤ ነገን ተስፋ አድርግበት፡፡ ዋናው ነገር መጠየቅን አለማቆም ነው፡፡
አልበርት አንስታይን
- አንድን ሃሳብ ሳይቀበሉት ማስተናገድ የተማረ አዕምሮ መገለጫ ነው፡፡
አሪስቶትል
- ሌሎች የተናገሩትን መድገም ትምህርትን ይጠይቃል፡፡ ሌሎች የተናገሩትን መገዳደር አዕምሮን ይጠይቃል፡፡
ሜሪ ፒቲቦን ፑሌ
- የህይወት እንቆቅልሾች በሙሉ የሚፈቱት በፊልሞች ላይ ነው፡፡
ስቲቨን ማርቲን
- ጥሩ ጦርነትና መጥፎ ሰላም፣ ኖሮ አያውቅም::
ቤንጃሚን ፍራንክሊን
- ሰው የተፈጠረው ለውድቀት ሳይሆን ለስኬት ነው፡፡
ሔነሪ ዴቪድ ቶሪዮ
Published in
ጥበብ