Saturday, 16 November 2019 11:16

“ፋሚሊ አርት ኤግዚቢሽን” ዛሬ በአዳማ ኤግል ሆቴል ይከፈታል

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(0 votes)

   የእውቁ ሰዓሊ ብሩክ ተሾመና የቤተሰቡ ስራዎች ለዕይታ የሚቀርብበት “ፋሚሊ አርት ኤግዚቢሽን” ዛሬ ከቀኑ 10፡00 ጀምሮ አዳማ በሚገኘው ኤግል ሆቴል ይከፈታል፡፡
በ1988 ዓ.ም ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አለ የጥበብና ዲዛይን ት/ቤት በቀለም ቅብ የተመረቀው ፕሮፌሽናል ሰዓሊ ብሩክ ግርማ የሳላቸው 50 ስዕሎች፣ ሁለት ቅርፃቅርፆችና ባለቤቱ ዲዛይነር ፍሬህይወት መንግስቱ በአበባ ዲዛይን የሰራቻቸው እቃዎች በድምሩ 62 ስራዎች ለእይታ ይቀርባሉ በተጨማሪም የሰዓሊውና የዲዛይነሯ ልጆች ኢዝል ብሩክ (ዳንሰኛ) ሶፎኒያስ ብሩክና የ10 ዓመቱ ልዑል ብሩክ (ድምፃዊ) ስራዎቻቸውን እንደሚያቀርቡ የታወቀ ሲሆን፤ የሰዓሊው የእህት ልጅ ዘሩባቤል አንተነህም በዚሁ አርት ኤግዚቢሽን ላይ እንደሚሳተፍ ለማወቅ ተችሏል፡፡
በመክፈቻ ሥነ ሥርዓቱ ላይ ሙዚቃና ዳንስን ጨምሮ በርካታ ኪነ-ጥበባዊ ክንዋኔዎች እንደሚካሄዱ የተገለፀ ሲሆን ሰዓሊያን፣ ገጣሚያን ዳንሰኞችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እንደሚታደሙና ኤግዚቢሽኑ ለአንድ ሳምንት ለእይታ ክፍት ሆኖ እንደሚቆይ ሰዓሊ ብሩክ ተሾመ ለአዲስ አድማስ ገልጿል፡፡  

Read 9584 times