Saturday, 16 November 2019 11:17

‹‹ነቃዮድ›› መጽሐፍ ሕዳር 7 ይመረቃል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(1 Vote)

 የደራሲ ቴዎድሮስ መዝገቡ ሦስተኛ ሥራ የሆነው ‹‹ነቃዮድ›› መጽሐፍ እሁድ ህዳር 7 ቀን 2012 ከቀኑ 8፡30 ጀምሮ በኢትዮጵያ ሆቴል ይመረቃል።
መጽሐፉ በዋናነት በቴክኖሎጂ ፈጠራና ዕፁብ ድንቅ ስለሆነው የጊዮን መግነጢሳዊ ምስጢር ላይ የሚያነጠነጥን ሲሆን በ301 ገጽ ተቀንብቦ በ152 ብር ለገበያ መቅረቡም ታውቋል። በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የተለያዩ ኪነ ጥበባዊ መሰናዶዎች ለታዳሚ የሚቀርቡ ሲሆን በመጽሐፉ ላይ ውይይትና ዳሰሳም ይካሄዳል ተብሏል፡፡
ደራሲው ከዚህ ቀደም ‹‹የአንድነት ጥሪ›› እና ‹‹ነቃ ማይ›› የተሰኙ መጽሐፍትን ለንባብ ማብቃቱ አይዘነጋም፡፡

Read 10335 times