Saturday, 23 June 2012 07:22

በአማርኛ የተሰራው የማራዶና ፊልም ዛሬ ይመረቃል

Written by  ግሩም ሠይፉ
Rate this item
(0 votes)

በዓለማችን የእግር ኳስ ታሪክ የማይረሳ ስምና ዝና ባለው አርጀንቲናዊው ዲያጎ አርማንዶ ማራዶና ላይ ወርቃማው ልጅ በሚል ርእስ ልዩ ዘጋቢ ፊልም በሃብትሽ ሶከር በአማርኛ ቋንቋ መስራቱ ታወቀ፡፡ ፊልሙ ዛሬ ከጠዋቱ 3 ሰዓት ላይ በእምቢልታ ሲኒማ የሚመረቅ ሲሆን በ20 ብር ዋጋ  ከዛሬ ጀምሮ  ለገበያ ይቀርባል፡፡ በሃብትሽ ሶከር የተሰራውን ዘጋቢ ፊልም የተረከው   ታዋቂው ጋዜጠኛ ሰለሞን ጓንጉል ሲሆን የማራዶናን አንዳንድ ታሪኮች ከፈረንሳይኛ ወደ አማርኛ የተረጎመው አንጋፋው የስፖርት ጋዜጠኛ ሁሴን አብዱልቀኒ ነው፡፡

ሃብትሽ ሶከር ከማራዶና በፊት የዚዳንና እና የሞውሪንሆ ዘጋቢ ፊልሞች  በሲዲ ለገበያ ማቅረቡ አይዘነጋም፡፡ ሃብትሽ ሶከር በቀጣይ የኢትዮጵያ ታዋቂ ስፖርተኞችን የህይወት ታሪክ ለማዘጋጀት ሃሳብ  እንዳለው ሲታወቅ የክርስትያኖ ሮናልዶ፤ የሊዮኔል ሜሲ እና የሮናልዲንሆን ፊልሞች ለመስራትም እቅድ ይዟል፡፡

 

Read 5482 times Last modified on Saturday, 23 June 2012 10:46