(ስለ ወጣቶች)
• በወጣቶች ላይ እምነት ይኑራችሁ፤ ዕድልም ስጧቸው፤ ያስደንቋችኋል፡፡
ኮፊ አናን
• ወጣቶችን ማነቃቃት ያስፈልጋል፤ ያሰቡትን ምንም ነገር ሊያሳኩ እንደሚችሉም ሊነገራቸው ይገባል፡፡
ጂም ስታይነስ
• ወጣቶች የሚያስፈልጋቸው አርአያ እንጂ ተቺ አይደለም፡፡
ጆን ዉድን
• ወጣቶች የነገ መሪዎች አይደሉም፡፡ የዛሬና የነገ መሪዎች ናቸው፡፡
ካቲ ካልቪን
• ወጣቶች ርዕይ ሲኖራቸው፤ አዛውንቶች ደግሞ ህልም አላቸው፡፡
ሬድ ስሚዝ
• ወጣቶች ህልም እንዳያልሙ ተስፋ ማስቆረጥ አይገባንም፡፡
ሌኒ ዊልኬንስ
• ዕድሜ የጠገቡ ሰዎች ሲታገሉ ወጣቶች ለሞት ይዳረጋሉ፡፡
አኔ ፎርትየር
• ለእኔ ሁለት ዓይነት ሰዎች አሉ፡- ወጣቶችና የኑሮ ልምድ ያካበቱ ሰዎች፡፡
ኤ.ፒ.ጄ. አብዱል ካላም
• አዛውንቶች መናገር፣ ወጣቶች ደግሞ ማዳመጥ መጀመር አለባቸው፡፡
ቶማስ ባንያክያ
• በቂ ተመክሮ ያላቸው ወጣቶች የሉም፡፡ የሕይወት ተመክሮን የሚፈጥረው ጊዜ ነው፡፡
አርስቶትል
• ወጣቶች እውነትን ለመናገር አይፈሩም፡፡
አና ፍራንክ
• ወጣቶች እብድ፣ እንግዳና ስሜታዊ ፍጡራን ናቸው፡፡
ኢቫን ግሎዴል
• ወጣቶች እምቢተኞች ብቻም አይደሉም:: የተለየ ልብም አላቸው፡፡
ግሎሪያ ትሬቪ