Saturday, 23 November 2019 12:13

‹‹Africa Future Summit Tour›› በአዲስ አበባ ተጀመረ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(1 Vote)

 የኢትዮጵያ ወጣት ወንዶች ክርስቲያን ማህበር (ወወክማ) ‹‹Africa Future Summit Tour›› በአዲስ አበባ ተጀምሯል፡፡ በአስር የአፍሪካ አገራት እንደሚካሄድ የተነገረለት ፕሮግራም ባለፈው ማክሰኞ ህዳር 9 በአዲስ አበባ አብነት አካባቢ ባለው የወወክማ አዳራሽ የተጀመረ ሲሆን ከ300 በላይ ታዳሚዎች መገኘታቸውም ታውቋል፡፡
በፎርብስ መጽሔት ከ30 ዓመት በታች ተሸላሚ ከሆኑ 30 ወጣቶች አንዷ የሆነችው ክርስቲያን ኒቲም፣ በፎርብስ መጽሔት ዋና የእድገት ባለሙያ የሆኑት ቶም ዴቪስ፣ የአፍሪካ ፊውቸር ፈንድ ሀላፊ ኢንስቲን ኒትም፣ የአፍሪካ አሊያንስ ወወክማ ዳይሬክተርና የአለም ወወክማ ተወካዮች ይገኙበታል፡፡ የዚህ ፕሮግራም አላማ ወጣቶችን ለስራ ፈጠራ ማነቃቃትና ከሌሎች አገራት ጋር የተሞክሮ ልውውጥ እንዲያገኙ ማድረግ ነው ተብሏል፡፡
የኢትዮጵያ ወወክማ ከተመሰረተበት 1942 ዓ.ም ጀምሮ በሚያካሂዳቸው የወጣቶችና የማህበረሰብ ልማት ላይ ያተኮሩ ፕሮግራሞች ሁሉንም ያማከለ የወጣቶች ተጠቃሚነትን ለማሳካት ሲሰራ የቆየ ሲሆን ወጣቶች በአዕምሮ በአካልና በመንፈስ ጠንክረው እንዲወጡ በማድረግ በአምስት ክልሎች በሚገኙ 10 ቅርንጫፎች፣ ከ10 ሺህ በላይ አባላትንና በጎ ፈቃደኞችን ይዞ፣ ከ30 ሺህ በላይ ለሆኑ የፕሮጀክት ተጠቃሚዎች ከመንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ጋር በቅንጅት የሚሰራ ማህበር ነው፡፡

Read 3208 times